ለግራዚያኒ ሀውልት መቆሙን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በዲሲ ተካሄደ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዲሲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ጣሊያንና ቫቲካን ኢምባሲዎች ፊትለፊት በመገኘት እ.አ.አ. በ1930ዎቹ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋ ለፈጸመው ሮዶልፎ ግራዚያኒ የመታሰሰቢያ ቤተመዘክርና የመናፈሻ ቦታ መሰየሙን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ግራዚያኒ በዓለም አቀፍ ስምምነት የተከለከሉና የተወገዙ የመርዝ ጋዝና ፈሳሽ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአውሮፕላን ላይ በማዝነብ በብዙ ሽህ ኢትዮጵያውያን ላይ የጅምላ እልቂት ፈጽሟል። ግራዚያኒ ከዚህም በተጨማሪ ሊቢያ ውስጥም ከፍተኛ እልቂት እ.አ.አ. በ1920ዎችም ውስጥ ፈጽሟል። በዚህም መሠረት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ለፈጸማቸው የጦር ወንጀሎች 19 ዓመት እስር ተበይኖበት እንደነበር ይታወቃል።

ለዚህ ዓለም በአለም ዓቀፍ ደረጃ “አራጅ” በመባል ለሚጠራው የቢኒቶ ሙሶሊኒ የቀኝ እጅ በመሆን በጦር ሚኒስትርነት ተመድቦ እጅግ ዘግናኝና የሰው ልጅ ይፈጽማቸዋል ተብሎ ለመናገር የሚዘገንኑ ማሳቃያዎችን ለፈጸመ ው የጦር ወንጀለኛ  ለአዶልፎ ግራዚያኒ በደቡባዊ የሮም ከተማ በሚገኝ ቦታ በአገሪቱ ግብር ከፋዮች ወጭ መታሰቢያ ተሰርቶለታል። ይህም የሚያሳየው በአሁን ሰዓት ጣሊያንን በማስተዳደር ላይ ያለው መንግስት ለኢትዮጵያውናንና ለሊቢያውያን ያለውን ንቀትና ጥላቻ ነው። ለምሳሌ ያህል ጀርመን ውስጥ ለአዶልፍ ሂትለርና ለተካታዮቹ መዘክር መስራት ይቅርና ስለናዚዎች በበጎ ሁኔታ ማንሳት እንኳ በህግ የተከለከለና “ውግዝ ከማሪዎስ” የሆነ ተግባር ነው። ሊደረግ ቢሞከር እንኳ ምን ያህል ዓለማቀፋዊ ትኩረትና ውግዘት በተለይም ከይሁዳዊያን እንደሚደርስ መገመት አያዳግትም። ለነገሩ ጀርመኖች እንኳን ይህንን ሊያደርጉና ሊያስቡት የሚችሉት ነገር እንኳን አይደለም። ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንደሚባለው ጣሊያኖች ይህንን እጅግ የሚያስቆጣ ወንጀል በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸሙት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ ባንዳና ለአገሪቱ የማይቆረቆር መሆኑ ስለሚያውቁ ነው።  ለዚህም ዋናው ማስረጃ ይህ መዘከር ከተከፈተ በኋላ የወያኔ አገዝዛ ያቀረበው ምንም ዓይነት ተቃውሞ የለም። እንደውም  አንድ ሰልፈኛ በስላቅ መልክ ሲናገሩ እንደተደመጡት ወያኔዎች ለጣሊያን መንግስት “እንኳን ሰራችሁ፣ በርቱ” የሚል መልዕክት ሳያስተላልፉ እንደማይቀር መጠርጠር ይገባል ብለዋል።

በሰልፉ ላይ የተነሱ የሚከተሉትን ፎቶግራፎች ይመልከቱ።

photo.JPGphoto.JPGphoto.JPGphoto.JPGphoto.JPGphoto.JPG

 

photo.JPGphoto.JPGphoto.JPG