ህጋዊውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያን ይቅርታ መጠየቅ አለብን
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ህጋዊውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ይቅርታ መጠየቅ አለብን
ከተድላ ጌትነት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ካሳለፈቻቸው ዘመናት ማለት ዘመነ ዮዲት ጉዲት ዘመነ ግራኝ ዘመነ ኢጣሊያ (የአምስቱ አመት ወረራ) የባሰ የመከራ ዘመን መግፋት ከጀመረች ድፍን 20 ዓመት ሆነ።የጉዲትም ሆነ የግራኝ ግልጽ ጠላትነት በመሆኑ አባቶቻችን የቻሉትን ቅርስና ንዋየ ቅድሳት በየዋሻውና በጉድጓድ ውስጥ በመደበቅ ጥቂት የማይባሉ ዘመን ተሻጋሪ ቅርሶችንና መንፈሣዊ እሴቶችን አቆይተውልናል። በዚያ ዘመን የነበረው ግልጽ ጥፋት ለመሸሽም ሆነ ለመደበቅ ዕድል ነበረው የአሁን ዘመን የአገሬ ሰው የወዳጅ ጠላት እንደሚለው አማኝ መስለው ይልቁንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከልና ቅርሶችንና መንፈሣዊ ሀብቶችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ቃል ገብተው የተሾሙ በትልቁና በወሣኙ ቦታ ላይ ሆነው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር የሚመዘብሩ አባ ጳውሎስ የቀደሞ ጠላቶች በግልጽ ሊያጠፉዋት ያልቻሉትን እርሳቸው በስውርና በግልጽ አወደሟት።
የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመንግሥት የሚቀርበው በፓትርያርኩ በኩል እንደሆነ ግልጽ ነው። ዛሬ መንግሥትን ስለ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይህን አደረግህ ይህን አጠፋህ ማለት አይቻልም። በእርግጥ አስቀድሞ የሚስማማውን መርጦ ማስቀመጡ ባይካድም ሥርዓቱን ጠብቆ ለመንግሥት የቀረበ ጉዳይ የለም። ይህም የሆነው አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ የሌላቸው ሆኖ አይደለም አብያተ ክርስቲያናትም ችገር ሳይገጥማቸው ቀርቶ አይደለም። በተለይም የእስልምና አክራሪ ቡድኖች አብያተ ክርስቲያናትን በየጊዜው ያቃጥላሉ አሁን እየተስራፋ ያለው ሃይማኖት የለሽ ትውልድ ሥልጣን በያዘበት ቦታ ሁሉ ቀደምት የቤተ ክርስቲያናትን ይዞታና ቅርስን መንፈሣዊ እሴቶችን ሁሉ በተቻለ አቅሙ ያጠፋል። ይህን ለመከላከል የሀይማኖት መሪው ግዴታ ነበር ነገር ግን እራሱን አጥፊና አውዳሚ በመሆኑ ጉዳት ደረሰ አልደረሰም ብሎ ሃይማኖቱን ወክሎ እራሱን አጥፊ (አውዳሚ) በመሆኑ ጉዳት ደረሰ አልደረሰም ብሎ ሃይማኖቱን ወክሎ ይጮሀል ልብ በሉ የዋልድባ መታረስ የዝቁዋላ መቃጠል ለአባ ጳውሎስ ደስታ ነበር። ለዘመናት የታወቁ ለአማኙ ሕብረተሰብ ብርቅዬ የሆኑት የገዳማቱ መጻሕፍት ዘመን ተሻጋሪ ታሪካችን ሀይማኖታዊ ዕውነታዎች ባህልና ሥልጣኔን አምቀው የያዙ በታሪክ ምሁራን የእውቀት መሥራቶች ለተመራማሪዎች የጥበብ ምንጮች የሆኑ ቅርሶች ይገኙበታል ምመናን ከቦታ ደርሰው ኃጢአታቸው ይሰረይላቸዋል። ወደነዚህ ቦታዎች የደረሱ ሁሉ የመንፈስ እርካታ ያገኛሉ የለመኑትን የተሳሉትን ሁሉ ያገኙባችዋል::
በአንፃሩ ትልቅ የካውንስሊንግና የህክምና ሆስፒታሎችን ወክለው በዘመን ያልተፈታ እንቆቅልሾችን እየፈቱ ከዘመን በኋላ ላለው ተስፋም ሰንቅ ሆነው ኖረዋል። የነዚህ ገዳማት ችግር ሁሉንም ትውልድ አንቀሳቅሷል። በእግራቸው ተጉዘው እሳቱን ለማጥፋት የደከሙ በቦታው ተገኝተው እያጠፉ ልማደኛው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲዋሽ አይተው አትዋሽ እሳቱ አልጠፋም በማለታቸው እግራቸው በጥይት ተመተው የቆሰሉም አልጠፉም። ይህ ችግር በሀይማኖቱ መሪ አፈቀላጤዎች ውሸት ነው ተብሎ ተነገረ በአይናችን አይተን መናገር እንኳን የማንችልበት ጊዜ ላይ መሆናችን በእርግጥም እየዘነጋነው ነው እንጂ ቆይቷል ፡፡
በእርግጥ እኔ ሳስበው ግን ህጋዊው ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቅሬዎስ ያለስማቸው ስም ሰጥተን ለቤተክርስቲያን አይጠቅሙም ብለን የተባለው ሰምተን ስናረጋግጥ እኛም ዝም አልን። አይደሉም የሚባልበት እድል በይኖርም እንኳን እውነቱን ተናግረን በሞትን ይሻለን ነበር፡፡ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የምእራባውያኑን ትራዲሽን ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱን ስርዓት ህግ ጠብቀው የቆዬ ግን የነበሩበት ዘመን ለመስራት የሚያስችል እድል የሌለበት በመሆኑም ስለቤተክርስቲያን መከራከር አይቻልም ነበር። ያም ሆኖ በጦርነት ቀጠናዎች እንኳን አፅናኝ አባት እየመደቡ እኛ ሐይማኖት እንጂ ፖለቲካ ምን አገባኝ እያሉ ጭንቁን ዘመን በጭንቅ አሳልፈውታል፡፡ በጦርነት የተያዙ ቦታዎች ጥለው ወደ መሀል አገር የመጡ አባቶችን ፡”ከማን ነው ተነጥላችሁ የመጣችሁት ያ እኮ ወገናችሁ፣ ልጃችሁ ነው” ብለው በማለታቸው ቂም ተቋጥሮባቸው መሀል አገሩን ወያኔ ሲቆጣጠረው ከወያኔ ቢሮ ሄደው ፓትርያሪኩ እንዲወርዱ ህዝቡ እዲያምፅ የተለያዩ ቅስቀሳዎች እንዲኖሩ ህዝቡ እንዲያምን ስልት ነደፉ። ወያኔ ውሸቱን እውነት ማድርግ የቆየ ብቸኛ እውቀቱ በመሆኑ ጊዜ ሳይወስድበት የሚባለው ሁሉ አስብሎ እንዲወርዱ ተደረገ ፡፡ ይህ ግፍ ሀሰት ሲነገር ዝም ብለን በማየታችን ቤተክርስቲን በጭንቅ የጠበቁት አባት በወሬ ሰምታችሁ ከጠላችሁ “በግልፅ ጥፋትን ታያላችሁ ዘመናችሁ የሀዘን ይሆናል” ብሎ ፈረደብን መሰል ለዘመናት አነባን። ይችን የታሪክ እውቀት የስልጣኔ አርማ የሆነችውን ቤተክርስቲን ውድቀት በዓይናችን አየን ጠላት ተሳለቀብን። ወዳጆች አፈሩብን እኛም አለቀስን። ዋልድባም ታረሰ አሰቦትም ተቃጠለ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ህገወጡ የወያኔው አቡነ ጰውሎስ ለሽርሽር ግብፅ ነበሩ። ህጋዊው ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሬዎስን ማንነት በአኗኗራቸውን መንፈሳዊ ህይወታቸውን ማየት ይቻላል፡፡ ነጋ ከፀሎት መሸ ከፀሎት ከሚተጉ አባቶች ዋነኛ እንደሆኑ ቀርቦ ማጣራት ይቻላል፡፡ አሁን ያለው መንፈሳዊ ህይወታቸው በአንድ ቀን የመጣ አይደለም። አብሮ የኖረ ነው እንጂ ችግሩ እኛ ሳናጣራ ስለምናወራ ሳናውቅ ስለምንጣላ ነው እንጂ መንፈሳዊ ህይወት በአንድ ጀንበር የሚመጣ አይደለም። ትላንትም እንዲህ ነበሩ በእርግጥም ስለአሳዘናቸው አዝነውብናል። ሀዘናቸውም እየጎዳን ስለሆነ ይቅርታ መጠየቁ ለእኛም የህሊና እረፍት ለቤተክርስቲያን እድገት ይሰጣል። መንፈሳዊ አባታችንን ነፃ እንውጣ። እግዚአብሔርም አባ ጳውሎስን በፍርዱ ከዲያቢሎስ አገልጋዮች ጋር ይደምርልን፡፡
አሜን
ተድላ ጌትነት
ባየር፣ ጀርመን