የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የምንል መልካም አጋጣሚው አሁን ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ገረመው አራጋው

በአገራችን ኢትዮጵያ አምባገነኑ የመለስ ስርዓት በስልጣን ላይ በቆየባቸው ባልፉት 20 ዓመታት ውስጥ  ኢሰብአዊ ኢዲሞክራሲያውዊ ኢፍታዊ ድርጊቶችን ሲፈፅምብን ቆይተናል::  ስርዓቱ ግን አንድም ጊዜ ከድርጊቱ ለመታቀብ አልሞከረም እኛም ከዚህ በደልና ጭቆና ለመላቀቅ እንዳንችል የተለያዩ አስፈሪ አዋጆችን መመሪያዎችን ድንጋጌዎችን እያወጠና እራሱ ላወጣው ህገ መንግስት እንካን ሳይገዛ ባደባባይ በተደጋጋሚ በማን አለብኝነት ከህግ በላይ እየሆነ እጅግ በጣም ብዙ ንጹሃን ዜጎችን ያስራል ያዋክባል ታሰቃያል ከሀገር እንዲሰደዱ ያደርጋል ይገላል  ወዘተ::  ህዝቡን በኑሮ ውድነት በመልካማ አስተዳደር እጦት በህግ የበላይነት አለመከበር በሙስና መንሰራፋት በዲሞክራሲያዎ መብቶች ባለመከበር በሚደርስበት በደል ስርዓቱ እጅ እጅ ብሎት  የዝሆን ጎሮ ይስጠኝ በማለት ድርጊቱን በሰፊው እየፈጸመ እያስፈፅመ ይገኛል::

ኢትዮጵያዊያን በሀገራችን ላይ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ባህል እንዲመጣና ከሚደርስብን ስቃይና መከራ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመላቀቅ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ  እጅና ጋንት ሆኖ መታገል የወቅቱ አንገብጋቢ ሁኔታ ሆኖ ተገኝታል::  የኢትዮጵያ ህዝብ እየደረሰበት ካላው በደልና ጭቆና ለመላቀቅ እሱ እራሱ እንጂ ባእዳንም ሆነ የባእዳን ጋሻ ጃግሬዎች አለመሆናቸውን ጠንቅቆ ያውቃል :: ህዝቡም እራሱን ከባርነት ቀንበር ሊያወጠ የሚችለው እራሱ ብቻ እንደሆን በማያሻማ መንገድ አረጋግጦዋል :: የሰብሃዊ መብቶች ተከራካሪ ተቃማት ጩከት እቤቱታ ዘገባና ተማጽኖ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም የፈየደለት ነገር የለም::  ይህንን የአምባገነን ስርዓት ከስልጣን ለማውረድ በሚደረገው የትግል ሂደት ሰላማዊ ትግል አስፈላጊነቱ የማያጠያይቅ ቢሆንም በሰላማዊ ሰልፍ በህዝባዊ አመጽ ካልተደገፈ የራሀብ አድማ የጾም ጸሎት የሻማ ማብራት የመሳሰሉት ተቃዎሞዎች ሁሉ ወደ አርህድ አንቀጥቅጥ ህዝባዊ ቁጣ እስካልተለወጠ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ይመጣል ብሎ ማሰብ የህልም እንጀራ ይሆናል:: ከእንግዲህ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግሉ አቅጣጫ አላማና ግብ የወያኔን አረመኔ ስርዓት ከስልጠን ማስወገድ መሆኑን ሊረዳው ይገባል::

ከአሁን በሃላ ወያኔን በምርጫ ሂደትና በሰላም ብቻ ታግለን ከስልጠን እናስወግደዋለን ብሎ ማሰብ የዋህነት ብቻ ሳይሆን ሞኝነትም ጭምር ነው::  ይህንን እውነታ ያልተገነዘቡ ግን በሰላማዊ ትግል ስርዓቱን እንቀለብሳለን ብለው የሚያምኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢያንስ የትግሉ እንቅፋቶች እንዳይሆኑ ከፍተኛ  ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል:: ይህንን እያወቁ ለወያኔ ከለላ እየሰጡ ወይንም ተለጣፊ እየሆኑ የህዝብን ትግል ለማምከን ጋሬጣ የሚሆኑት ክፍሎች የወያኔ አባሪ ተባባሪ እንደሆኑ ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል:: በዚሁ ስር ነቀል የትግል እንቅስቃሴ ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ዋና ጠላት መሆኑን ተረድተው ይህንን  የእናት ቱት ነካሽ የሆነውን አረመኔ ስርዓት ለመጠል ማንኛውንም መሰዋትነት ለመክፈል ታግለው ህዝቡን ለማታገል የተዘጋጁ ሊሆኑ ይገባል::  አገራችን እረጅም ጊዜ ታሪክ ወያኔን የመሰለ የወገን ጠላት አጋጥሞት እንደማያውቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል::  ይህንን ዘረኛ ቡድንና የወገን ጠላት አስፈላጊው መስዋትነት ተከፍሎ ከስልጠን ከማስወገድ በስተቀር ሌላ አማራጭ የሌለ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቃል::

ዛሬ በዲሞክራሲ አደጉ የምንላቸው ምዕራባዊያን መለስን በምስራቅ አፍሪካ እንደ ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ ስለሚጠቀሙበት ብሎም ምንም አይነት የዲሞክራሲ ስርአት ያልገነቡት ቻይናና ህንድ ለተፈጥሮ ሀብት እንደልባቸው መዝረፍ እንዲመቻቸው   ከወያኔ ጋር ስለተባበሩ የኢትዮጵያ ህዝብ በአምባገነኑ መለስና ለሆዳቸው ባደሩ ቡችሎች እየደረሰበት ያለውን ስቃይና መከራ እንግልት ከራሱ ከኢትዮጵያ ህዝብ በስተቀር ሊረዳው  የቻለ የውጭ ሃይል አልተገኝም::   ምዕራብያዊያንም ሆኑ ሌሎች ቡድኖች ለራሳቸው ዘላቂ ጥቅም ብቻ ሲባል ወያኔን እንደ መሳሪያ በመጠቀም ለኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ስቃይና መከራ አባሪ ተባባሪ ሆነዋል ህዝባችንም ስቃይና በደሉን ሰሚ አጥቶ ወደ ፈጣሪው አቤቱታውን በማሰማት ላይ ይገኛል::

በአሁኑ ወቅት የወያኔን ዘረኛና ፋሽስታዊ የአገዛዝ ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስለጣን ለማስወገድ በመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄዎች ከሁሉም አቅጣጫ እየጎረፈ ይገኛል::  ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የወያኔን የማፊያ ስርአት ከጫንቃችን ላይ አስወግደን እኩልነት: ፍትህ: ዲሞክራሲና: እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌላው ግዜ በበለጥ መረባረብ አለብን::