ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“…ኢሕአዲግ ከገባበት የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ ለመውጣት የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦችንና ሕዝቦች እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚያደርገው ሙከራ በሕዝባችን በተባበረ ትግል ይከሽፋል!…”
=======

ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

“…ኢሕአዲግ በ1983 ዓ.ም ከደርግ ስርዓት ውድቀት በኋላ የመንግስት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ከእስራት፣ ከአፈና፣ ከስደት እና ግድያ እፎይ ብለው ያሳለፉት ወቅት የለም፡፡

Image may contain: 5 people

በነዚህ ረዥም የሕአዲግ የአገዛዝ ዓመታት ከጫፍ ጫፍ በአራቱም ማዕዘናት የሚኖሩ ህዝቦች ኢሕአዲግ የሚያደርስባቸውን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰቶች ሲቃወሙ ቆይትዋል፡፡ “ከእኔ ወዲያ ለዚህች ሀገር እና ህዝብ ተቆርቋሪ የለም” በማለት የሚመፃደቀው ኢሕአዴግ ይህን ግፍ እና በደል በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲፈጽም የኖረው ራሱ አዘጋጅቶ ያጸደቀውን ሕገመንግስት እየጣሰ ነው፡፡

በዚህ ድርጊቱም በተለያዩ ወቅቶች በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች – በወላይታ፣ በሀዲያ፣ በቡርጂ፣ በጌድኦ፣ በሲዳማ፣ በከምባታ ጠንባሮ፣ በኮንሶ፣ በደራሼ፣ በየም ብሔረሰብ፣ በመንጃ ህዝብ፣ በሸኮ መዥንገር ህዝብ፤ በጋንቤላ ክልል በአኝዋክ ብሔረሰብ ላይ፤ በቤንሻንጉል ህዝብ፣ በትግራይ ክልል ህዝቦች፣ በሶማሌ ክልል ህዝዝቦችና በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን ግፍና ጭቆና አድርሷል፡፡

በአሁኑ ጊዜም በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ሕገመንግስታዊ መብታቸውን ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ ሰልፍ የወጡትን ዜጎች – ህጻን፣ ሽማግሌ፣ አሮጊት ወዘተ ሳይለይ በመጨፍጨፉ ኢ-ሰብኣዊ ድርጉቱን የአለም ሕብረተሰብ የጉድ ጉድ እስከ ማለት ደርሷል፡፡

መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም የኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓል የሆነውን የኢሬቻ ስነስርዓት ለማክበር በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ ሀይቅ በተሰባሰበው ከሚሊዮን በላይ በሆነ ሕዝብ ላይ በኢሕአዴግ ታጣቂዎች በተከፈተው የማሸበር እርምጃ በመቶዎች በሚቆጠሩ ወገኖቻችን የሞትና በሺዎች በሚቆጠሩ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ፣ የኢሕአዴግ ስርዓት ጨርሶ ቀልብ ያጣ ፀረ-ሕዝብ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህ በኢሬቻ በዓል ላይ ለደረሰው የሕዝብ ዕልቂት ሃላፊነቱ የኢሕአዴግ መሆኑን መድረክ እያስገነዘበ፣የተከሰተውንም ሁኔታ ገለልተኛ የዓለም አቀፍ አካል ተቋቁሞ እንዲያጣራ መንግስትን ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም ለአደጋው መድረስ ምክንያት በሆኑት ባለሥልጣናትና የደህንነት አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲወስድ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችም ካሳና መቋቋሚያ እንዲከፍል በአፅዕኖት እንጠይቃለን፡፡

በየአከባቢው የሕግ የበላይነት እና መልካም አስተዳደር ጠፍቶ የኢሕአዲግ ካድሬዎች ብልሹውን የኢሕአዲግ ስርአት መከታ በማድረግ በሙስና ባህር በመዋኘት የኢትዮጵያን ሕዝቦች ሀብት ዘርፈዋል፣ መዝብረዋል፤ ጥቂት ኢሕአዲግን የተጠጉ ቡድኖች ከምንም በመነሳት ቢሊየነሮች በመሆን፣ ሀብት በማከማቸ

ት ለከንቱ የመንደላቀቅና የብክነት ኑሮ እንዲበቁ ተደርገዋል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ለከፋ ድህነት ተጋልጠው፣ ከሞቱት በላይ፣ ከቆሙት በታች የሚሉት አይነት ኑሮ ለመኖር ተገደዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ሰማይ ጣሪያ በታች የሚፈጸመው ይህ ዘርፈ ብዙ ጭቆና፣ ግፍ እና መድልዖ ጽዋው ሞልቶ በመፍሰሱ ምክንያት ሕዝባዊ እምቢታ በመቀጣጠሉ፤ ኢሕአዲግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሕዝባዊ ተቃውሞ ማእበል ውስጥ እየተናጠ ይገኛል፡፡

በዚህ የተደናገጠው ኢሕአዲግም እንደ ልማዱ “የመልካም አስተዳደር እና የተሀድሶ ግምገማ እያካሄድኩ ነኝ፣ በዚህም ለውጥ አመጣለሁ” በማለት የተጨፈኑ ላታላችሁ ዓይነት የማዘናጊያ ዘዴዉስልቱን እየተጠቀመ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ከገባበት የፖለቲካ አጣብቂኝ የሚወጣ መስሎት ወደ ከፋፍለህ ግዛ ስልቱ በመመለስ፣ ብሔር ብሔረሰቦችን እርስ በእርስ ለማጋጨት እና ለማቃቃር በማቀድ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጉራጌ፣ በሐዲያ እና ከንባታ ጠንባሮ ዞኖች የሚኖረው ሕዝብ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንዲያወግዝ በካድሬዎቹ የተጠራው ስብሰባ፣ በተሰብሳቢው ሕዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
በሀዋሳ ከተማ እና አከባቢውም ተመሳሳይ አላማ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ታቅዶ እንደነበር ሲታወቅ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እድል አግኝቶ አደባባይ ከወጣ ተቃውሞ

ውን ወደ ኢሕአዴግ እንደሚያዞር በመሰጋቱ እቅዳቸውን እንደሰረዙ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ኢሕአዲግ በየጊዜው የአማራን ብሔር ከትግሬ፣ የኦሮሞን ብሔር ከአማራው ለማጋጨት ደፋ ቀና ሲል የቆየበት ስልት አልሳካ ማለቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከቅርብ ቀናት በፊት ደግሞ የኦሮሞን ህዝብ እና የአማራን ሕዝብ ከሶማሌ ሕዝብ ጋር ለማጋጨት የበሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳውን በሞኖፖል በያዛቸው የመገናኛ ብዙሃን ሲያጧጥፍ ሰንብቷል፡፡

በዚህ ወቅትም በአማራ እና በኦሮሞ ህዝብ ላይ በማነጣጠር በሶማሌ ክልል በጅጅጋ ከተማ ካድሬዎች ሕዝቡን አስገድደው ሰላማዊ ሰልፍ በማስወጣት “ኦሮሞ ጠባብ ነው፣ አማራ ትምህክተኛ ነው ወዘተ” የሚሉ አስነዋሪ መፈክሮችን አስይዘው ለእኩይ ዓላማቸው ድጋፍ ለማግኘት ሙከራ አድርጓል፡፡
በግዳጅ በተጠራው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፣ ለጥቅማቸው ሲሉ ነፍስ እና ስጋቸውን ለሕወሃት/ኢሕሀዲግ በማስገዛት በገዛ ሕዝባቸው ላይ ቁማር እየተጫወቱ ያሉት የክልሉ ከፍተኛ ካድሬዎች፣ የቀድሞ የኢሕአዲግ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ በሽግግሩ መንግስት ወቅት ወደ ሶማሌ ክልል በመሄድ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረገውን አይነት የጥላቻ ቅስቀሳ በአዲስ መልክ አሰምተዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ከፍተኛ ካድሬዎች ተመቸን ብለው የሚመጻደቁበት የፌዴራል ስርዓት ተብየው በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች እንዳለው ያለ የኢሕሀዲ

ግ የሞግዚት አስተዳደር እንጂ ከዚያ የተለየ ላለመሆኑ በክልሉ አስተዳደር እና የደህንነት ጥበቃ አካላት ላይ በተደጋጋሚ በፌዴራል መንግስት ይደረጉ የነበሩ ብወዛዎችና ተጽኖዎች እንዳሉ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ የክልላዊ የራስ ገዝ አስተዳደር ነፃነት እና የፍትህ እጦት ገፈት ቀማሽ የሆነው ሰፊው የሶማሌ ክልል ሕዝብ የተመረረበት ጉዳይ ነው፡፡

ስለሆነም የሶማሌው ክልል ጭቁን ህዝባችን ከጨፍጫፊው እና መዝባሪው ስርዓት ጎን በደጋፊነት በመቆም፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለፍትህ እና ለትክክለኛ ፌዴራሊዝም ስርዓት መስፈን መስዋዕትነት በመክፈል ላይ የሚገኙ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ትግል የሚያወግዝበት አንዳችም ምክንያት እንደማይኖር መድረክ ያምናል፡፡

በመሆኑም ለዘመናት በአብሮነት ተከባብረው የኖሩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ ኢሕአዲግ እና ካድሬዎቹ የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም የሚያደርጉት የፖለቲካዊ ሸፍጥ አካሄድ እና ተንኮል እንዳይሳካ በመካከላቸው ያለውን የአንድነት ስሜት ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲያጠናክሩ መድረክ ለመላ የኢትዮጵያ ሕ

ዝቦች ጥሪ እያደረገ፣ ለኢሕአዲደግ እና ካድሬዎቹም፤ ሕዝብን ከሕዝብ እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚያደርጉት መሰሪና ፀረ አንድነት እንቅስቃሴ ጊዜ ይፍጅ እንጂ እነርሱም ቢሆኑ ተጎጂዎች እንጂ ተጠቃሚዎች እንደማይሆኑ ተገንዝበው ከአፍራሽ እንቅስቃሴአችው እንዲቆጠቡ መድረክ ያስገነዝባል፡፡

መላው የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችም፤ ሀ

ገራችንን ከገባችበት የፖሊቲካ አዘቅት ለማውጣት ያለው ብቸኛ አማራጭ፣ በዘርና በሀይማኖት ሳይከፋፈሉ እጅ ለእጅ ተያይዘው አንድነታቸውን አጠናክረው አንባገነናዊውን ስርዓት በሰላማዊ አግባብ ታግሎ በማሸነፍ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን መገንባት መሆኑን እናስገነዝባለን፡፡

በመጨረሻም፣ ኢሕአዲግ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ከሚለው የብቸኛ አውራ ፓርቲ አምባገነንነት ቀኖና ተላቅቆ፣ ከፓርቲ ጥቅም ይልቅ የሀገርን እና የሕዝብን ጥቅም በማስቀደም ከመድረክና ከሌሎች ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የፖለቲካ ምህዳሩን ለማደላደል እና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ተደራሽ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ ድርድር ውስጥ እንዲገባ መድረክ በኢትዮጵያ እና ዜጎቿ ስም ለኢሕአዴግ ሀገራዊ ጥሪ ዳግመኛ ያደርጋል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ ባለድርሻ የሆነው አለማቀፉ ለጋሽ መንግስታትም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ፈታኝ እና ለሀገራችን ህልውና አደገኛ የሆነውን ሁኔታ በአንክሮ በመገ

ንዘብ፣ ኢሕአዴግ ከሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ወደ ድርድር እንዲገባ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ እናደርጋለን፡፡

• ድል ለሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ትግላችን!
• ክብር ለመብቶቻቸው ሲታገሉ ለተሰዉት ዜጎቻችን!
• ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም

አዲስ አበባ…”