የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ፣ ፀደቀ ድጋፌ እና አዲስአለም ደስታ በሁከት ማነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው በትላንትናው እለት ታስረዋል፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ፣ ፀደቀ ድጋፌ እና አዲስአለም ደስታ በሁከት ማነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው በትላንትናው እለት ታስረዋል፡፡ ትላንት ከስራ ሰዓት በኋላ በላሊበላ ሬስቶራንት ተገናኝተው ሻይ ቡና እያሉ በሚጨዋወቱበት ወቅት ነው ከምሽቱ 1፡30 ላይ እዛው ሬስቶራንት በነበሩ ሲቪል የለበሱ የፓሊስ አባላት ተይዘው 6ኛ ፓሊስ ጣቢያ የታሰሩት፡፡
ዛሬ ጠዋት ላይ ሶስቱም ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን የቀረበባቸው ክስ “ላሊበላ ሬስቶራንት ሆነው መንግስት በቢሾፍቱ የኢሬቻ አክባሪዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ትክክል እንዳልሆነ በዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች ለተቃውሞ እንዲነሳሱ በሚያደርግ መልኩ ሲያወሩ ነበር “ የሚል ነው፡፡ በዋስትና እና ምስክሮች ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስማት ነገ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ቄራ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡