የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለ ልዩነትና በአንድ ዘር ስለተደራጀ ወታደራዊ ገዳይ ጦር ሊሰማ ሊያይ ኣይገባም። ቆንጂት ስጦታው
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ቆንጂት ስጦታው — የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለ ልዩነትና በአንድ ዘር ስለተደራጀ ወታደራዊ ገዳይ ጦር ሊሰማ ሊያይ ኣይገባም። ይህንን የሚመኙለት ካሉ ኣንድም እድገትና ኣንድነት ፍቅርና እኩልነት የማይፈልጉ ሕዝብን ለማናከስ የሚጥሩ ኣልያም ልክ ሕወሓት በኣንድ ዘር ወጥ ምልምል ኣድርጎ በሰራቸው የኣግዓዚ ኮማንዶዎች ኣይነት ሌላ ኣዲስ የዘር ጭፍጬፋና እልቂት የሚመኙ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ጭፍጨፋ ማቆም የለበትም ብለው የሚያልሙ ቅዥታም ዘረኞች ናቸው። ሕወሓት የትግራይ ተወላጆችን ሰብስቦ በመሰረተው የኣግዓዚ ጦር እየደረሰ ያለው እልቂት ትምህርት ሊሆነን ይገባል።
ኢትዮጵያንን ያቀፈ ጠንካራ የእኩልነት መንግስት እንዲመሰረት ዜጎች በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውረው የመኖርና የመስራት ሕልውናቸው እንዲረጋገጥ የሃገሪቱ ጦር ለስልጣን ጥመኞች ሳይሆን ለሕዝቦች ጥቅም የሚውል እንዲሆን መንግስት ሕዝብን እንዲያዳምጥ ጨፍጫፊው የሕወሓት ኣገዛዝ እንዲወገድ ሁላችንም የጀመርነውን ትግል ልንቀጥል ይገባል። ባረጀና ባለፈበት የዘር ፖለቲካ መጠመድን ኣቁመን የጀመርነውን የኣንድነት ትግል በድል በማጠናቀቅ ሕዝቦች በእኩልነት ካለኣድልዎ የሚኖሩባትን ኢትዮጵያን ልንመሰርት ይገባል።
ቆንጂት ስጦታው