የኢሬቻውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ህዝብ የተቃውሞ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወያኔዎች አይናቸው እያየ ታሪክ ሰርተን አይናቸውን እናፈርጠዋለን። #Ethiopia

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ህዝቡ ነገ እንቅስቃሴ እንደማይኖር እየተናገረ ነው፤ በኣስጎሪና በሰበታ በርካታ ፋብሪካዎች ጋይተዋል። የወያኔ ውሾች በኣለም ገና ፈሰዋል። በኣቃቂ ቃሊቲ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነው። ወያኔ ጭንቅ ውስጥ ገብቷል ። ጸረ ሰላም ካለቸው የግብጽ ተላላኪ ብሎ ከፈረጃቸው ጋር እንዲያደራድሩት ኣዲስ ኣበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችን ኣማላጅነት እየላከ ነው።በሻሸመኔ በትግሬው ሕወሓት ወታደሮችና በሕዝቡ መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በሕወሓት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ታውቋል። የኢሬቻውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ህዝብ የተቃውሞ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፤ በወንጂ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ እርሻ በሦስት አቅጣጫዎች የአካባቢው ገበሬዎች እሳት ለቀው ቃጠሎ መነሳቱንና በፈጣን ሁኔታ እየተቀጣጠለና እየተዛመተ ነው፡፡

በምዕራብ አዲስአበባ መውጫ በጂማ በር ካራቆሬ አዋሳኝ – በወለቴ አንድ ማደያ ሲቃጠል፣ በዓለምገና ከተማ የመንግስትና የአይካ ጭርቃጭርቅ ፋብሪካ መኪናዎች ተቃጥለዋል፡፡ የዓለም ገና ት/ቤቶች ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ ታፍሰው ታስረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ በአዲስ አበባ ሁሉም መውጪያና መግቢ አቅጣጫዎች ውጥረት ነግሷል፡፡ ህዝቡ ነገ እንቅስቃሴ እንደማይኖር እየተናገረ ነው፤ ወጣቶች ነገ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የአየርጤና ት/ቤት ተማሪዎች በፌደራሎች ታፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡ሕዝቡ አሸናፊነቱን በተግባር እያሳየ ነው ትግሉ ቀጥሏል። #ምንሊክሳልሳዊ

Image may contain: outdoor, one or more people and nature