“የመቀሌ-ሸሬ መንገድ ሁመራ ድረስ መሄዱ ተከልሶ ከወረታ-መተማ ድረስ ያለው ጸደቀ” እያሉ በሬ ወለደ ጸረ-አማራ እንቅስቃሴ ጀምረዋል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የኢትዮጵያ ምድር ባቡርን በተመለከተ አማራ ክልል ውስጥ በሁለተኛው ዙር ሊሰሩ ከታቀዱ መስመሮች ውስጥ አንዱ የወረታ- አዘዞ-መተማ (መስመር 7) ነው። በዚሁ ዙር በትግራይ በኩል ደግሞ ከመቀሌ-ሽሬ ይገነባል ተብሎ ታቅዱዋል። አንድ ለአማራ እጅግ አንገብጋቢ የሆነ ጉዳይ አለ። በአጭሩ እንደሚከተለው እገልጸዋለሁ። ተስፋኪሮስ አረፈ (https://www.facebook.com/search/top/…) የተባለ ግለሰብና እና ጉዋደኞቹ ይሄን ሳምንት መነጋገሪያ ብለው በትግርኛ እንደ አጀንዳ ከያዙት ጉዳይ አንዱ (አሁን የኦሮሚያውን ጉዳይ ተከትሎ ለሚቀጥለው ሳምንት አዙረውታው) “የመቀሌ-ሸሬ መንገድ ሁመራ ድረስ መሄዱ ተከልሶ ከወረታ-መተማ ድረስ ያለው ጸደቀ” እያሉ በሬ ወለደ ጸረ-አማራ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የዚህ እንቅስቃሴ ዋና መነሻ ግን ያገር ውስጥ የባቡር መንገዱ ሳይሆን፣ አማራ ክልል በሁለት በኩል (ከሱዳንና ከጅቡቲ ጋር) ከውጪ የሚዋሰን ሲሆን ትግራይ መውጫ አልተሰራላትም ከሚል ጭንቀት የመነጨ ነው። ከዚህ ሁሉ ጀርባ ያለው ትልቁና ማሰናከል የሚፈልጉት ግን በተባበሪት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽንና በአፍሪካ ባንክ ታግዞ ሊሰራ የታቀደው ከካይሮ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያቁዋርጥ የትራንስ አፍሪካ የባቡር ሃዲድ በአሁን እንደታቀደው በአማራ ክልል ሳይሆን በትግራይ በኩል እንዲያልፍ ለማድረግ የታቀደ ሴራ ነው። እነኚህ ሰዎች ከ FB በዘለለ በአካል ለመደለል (to lobby) በትግርኛ እየተነጋገሩ ይገኛሉ። የትራንስ አፍሪካ የባቡር ሃዲድ አሁን ባለው እቅድ መተግበር በአማራ ህዝብ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት ነፍስ የሚዘራ ትልቅ ትርጉም ያለው እቅድ ነው። እነኚህ ሰዎች ለማኮላሸት የሚያደርጉትን የ FB ዘመቻም ሆነ የአካል ድለላ እናንተ የአማራን ጥቅም ለማስከበር ዘብ እንደቆመ ድርጅትም ሆነ እንደ ግለሰብ፣ እኛምዚሁ እንደምንችለው ይህን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተልን እንደ አስፈላጊነቱ በተደራጀ መልክ ለመልስ ምት መዘጋጀት ይኖርብናል የሚለውን ልጠቁም እወዳለሁ ። ከዚሁ ጉዳይ ጋር ወደ ተያያዙ መረጃዎች የሚወስዱ አንዳንድ ማስፈንጠሪያዎች ከዚህ በታች አስቀምጫለሁ። ድል ለጭቁኑ የአማራ ህዝብ። https://www.facebook.com/search/top/… http://www.erc.gov.et/…/national-railway-network-of-ethiopi… http://hornaffairs.com/…/update-ethiopia-new-railway-phase…/ https://en.wikipedia.org/wiki/Trans-African_Highway_network
