ህወኃት የጥፋት ኃይሎች እያሰማራ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ህወኃት የጥፋት ኃይሎች እያሰማራ ነው::
በተለያዩ ወንጀሎች በእስር ቤት የቆዩ ‹ወጣቶችን› በጥቅም በመደለልና በማሰልጠን በዓለም ገና፣ ሰበታ አካባቢ ያሉ የሌላ ክልል ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ለማድረስና የኦሮሞ ወጣቶች እንዳደረጉት በማስመሰል የህዝብ ለህዝብ ግጭት እንዳለ ለማሳየት፣ መተማመንና አንድነት እንዳይኖር ፣ ጥርጣሬ እንዲነግስና የትግል አንድነት እንዳይኖር ህወኃት የጥፋት ኃይሎችን ማሰማራቱን የአካባቢው ምንጮች አሳውቀዋል፡፡
እነዚሁ ምንጮች አክለው ይህ የጥፋት ድርጊት በተለይ በአማራ ነዋሪዎች ላይ እንዲያተኩርና በአማራና በኦሮሞ ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን የትግል-አንድነት ኦሮሞው ‹‹ የአማራ ደም – ደሜ ነው›› አማራው ‹‹የኦሮሞው ደም- ደሜ ነው›› የማለታቸው በህወኃት የፈጠረው ጭንቀትን ለማርገብ የተጠነሰሰ ሴራ … መሆኑ ታውቆ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ህዝብ እንዲያውቀው በማለት አሳስበዋል፡፡
በተመሳሳይ በአካባቢው ያሉ የለውጥ ኃይል ታጋይ ወጣቶች ይህ የጥፋት ሴራ የተወጠነው በኦሮሞ ስም በሌሎች ብሄረሰቦች ሥጋት በመፍጠር ‹‹ያለ ህወኃት መከታ የለንም›› በሚል ድጋፍ ለማሰባሰብ ስለሆነ ማንም የዚህ ሴራ ሰለባ እንዳይሆን አስጠንቅቀው- ትግላችን ከህወኃት ጋር ነው፣ ከህወሃት ዘረኞችና ከእነርሱ ጉዳይ ፈጻሚና አስፈጻሚዎች ውጪ በማንንም ኢትዮጵያዊ ብሄር ጋር ችግር እንደለሌብን እንዲታወቅ በማለት መልዕክታቸውን አድርሰዋል፡፡