ወያኔ በቢሾፍቱ የጨፈጨፋቸው ወገኖች ቁጥር ከ500 በላይ ሆነ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ቢሾፍቱ እየተከበረ ባለው የእሬቻ በዓል ላይ የሞቱት ቁጥር ከ500 በላይ እንደሆነ ተዘገበ:: ቁጥሩ በየሰዓቱ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖችም መቁሰላቸውን ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች ገልጸዋል። በዚህ የ እሬቻ በዓል ላይ በአብዛኛው ሕይወታቸው የጠፋው ወገኖች ኦሮሞዎች እና አማሮች መሆናቸው ተገልጿል:: የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሰላም የ እሬቻን በዓል እያከበረ ባለው ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ሲጨምር ሂሊኮፕተርና መትረየስ ተጠቅሟል:: አፍቃሪ ሕወሓት የሆኑ የመንግስት ድረገጾች ሂሊኮፕተሮች ወረቀት እየበተኑ ነበር ይበሉ እንጂ ሂሊኮፕተሮቹ አስለቃሽ ጭስ እየበተኑ በመትረየስ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ሕዝቡን ፈጅተውታል።
ንፁሃንን ገድሎ አፋልጉኝ ማለት ልማዱ የሆነው ወያኔ ወገኖቻችንን በግፍ ጨፍጭፎ የሀዘን ቀን ማወጁ ምን ማለት ነው? በእርግጥ በሀገራችን ግፉና መከራው አልበርድ ብሎናልና መሪር ሀዘን ልናዝንና ልንጾም ልንጸልይ ይገባናል፤ይሁን እንጅ በእሬቻ በአል አከባበር ላይ ለደረሰው እልቂት ተጠያቂው ወያኔ ብቻ ነው።
አሰግድ ታመነ