በደቡብ ኦሞ– ሰላማዊ ሰልፎች – ተጨናገፉ፣ ዕቅዶች ተሰረዙ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በደቡብ ኦሞ– ሰላማዊ ሰልፎች – ተጨናገፉ፣ ዕቅዶች ተሰረዙ
1. ሳላማጎ ወረዳ ዋና ከተማ ሃና ልማቱን በመደገፍ-በአማራ ኦሮሚያና ኮንሶ የሚደረገውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የመንግስትን የልማት ስራ ለማደናቀፍ፣ በጥቂት ፀረ-ልማት ኃይሎች የተቀነባበረ ነው በማለት ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ከዞን በወረደ መመሪያ በመስከረም 13 /2009 የታቀደው ሰልፍ በካቢኔዎች ስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ለ14 /01/09 –ተላልፎ በሁለተኛው ቀንም ካቢኔው አሁን በምንሰማው አገራዊ ሁኔታ ለመንግሰት የድጋፍ ሰልፍ ውጡ፣ የመብት ጥያቄ ያነሱትን ተቃወሙ ብለን ነገ አብረን ከምንኖረው ህዝብ ፊት ለመቅረብ አይቻለንም፣ በማለት ከዞን የወረደውን ትዕዛዝ ለመፈጸም ባለመስማማታቸው ተሰርዟል፡፡
ይህ ወረዳ ወደ ምርት የማይገቡት የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የሚገኙበት ወረዳ ነው፡፡


2. ለተመሳሳይ ዓላማ በ14/01/09 በጋዘር/ ደቡብ አሪ ዋና ከተማ/ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍም አንድም ሰው ከቤቱ ባለመውጣቱ ሊካሄድ አልቻለም፡፡ በንግድ ቤቶች በረንዳ ቆመው የገጠር ነዋሪው ከመጣ በሚል ሲጠባበቁ የነበሩ የወረዳና የከተማዋ ካቢኔ አባላትም ድምጻቸው ሳይሰማ ወደ መሸታ ቤትና መኖሪያቸው ተመልሰዋል፡፡ የዚህ ደቡብ አሪ ወረዳ አርሶአደሮች የመንግስት ግብርና የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ብድር ከአምና ጀምሮ አንከፍልም ማለታቸው ከዚህ በፊት መገለጹ ይታወሳል፡፡


ይህን የተመለከተው የዞኑ መስተዳድር በሌሎች ወረዳዎችና በጂንካ ከተማ ለማድረግ ያሰባቸውን ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፎች መሰረዙን ፣ በጂንካ ከተማ ቀድሞውኑ ሰላማዊ ሰልፉ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነት ሊቀየር ይችላል በሚል ስጋት ከሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች በኋላ እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡