­

ከደብረ ማርቆስ ከተማ 38 ኪሎ ሜትር የቦቅላ ከተማ በተኩስ እየተናጠች ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ትናንትና ዛሬ በየቦቅላ የአማራ ተጋድሎ እየተካሄደ ነው። የቦቅላ ከደብረ ማርቆስ ከተማ 38 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የገጠር ከተማ ነች። ወደ የቦቅላ የሚያስገባውና የሚያስወጣው መንገድ እዚህ መግለጥ በማልፈልገው ቦታ ስለተዘጋ ከትናንትና ጀምሮ ወደ የቦቅላ ምንም ዓይነት ተሽከርካሪ መግባትም ሆነ መውጣት አይችልም። ባሁኑ ሰዓት ከተማዋ በተኩስ እየተናጠች ነው። ዛሬና ትናንትና በነበረው ህዝባዊ ተጋድሎ «ወያኔ ሌባ!»፤ «ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!»፤ «የአማራ ደም ፈሶ አይቀርም!» በማለት አማራ ከዳር እስከ ዳር ተነስቶ ከወያኔ ራሱን ነጻ ያወጣ ዘንድ ጥሪ አስተላልፈዋል። (Achamleh Tamiru)