ኢ ህገ-መንግሥታዊ የደቡብ ክልል የብሔሮች ብሔረሰቦች መብት ጥያቄ አፈና ልምድ ለኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ትርምስ መነሻ እየሆነ መጥቷል፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
– ለኢትዮጵያ ሕዝቦች በሙሉ
– ለኢህአዴግ አራቱ እህት ድርጅቶች
– ለሁሉም አጋር ድረጅቶች በሙሉ
– ጭቆናን ለማሹ ለዓለም ማሕበረሰብ በሙሉ
ባሉበት ሁሉ
ኢ ህገ-መንግሥታዊ የደቡብ ክልል የብሔሮች ብሔረሰቦች መብት ጥያቄ አፈና ልምድ ለኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ትርምስ መነሻ እየሆነ መጥቷል፡፡
እንደሚታወቀው በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል መንግሥትን ያዋቀሩት 56 ማንነታቸው የተረጋገጠላቸው ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች መሆኑ እሙን ነው፡፡ እነዚህ ብሔረሰቦች ሕዝቦች በክልሉና በፌዴራል ሕገ መንግሥታት አንቀጽ 39/3/ መሠረት እራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት ከመጎናጸፈቻውም ባሻገር በክልሉና በፌዴራል ህገ መንግስታት ውስጥ የተከበረላቸውን መብቶች እንዲቀጠሙ ዋስትና አግኝተዋል፡፡
በክልሉ የማንነት ጥያቄ ከተመለስ በኋላ ለብሔረሰቦች የሚሰጠው የአስተዳደር መዋቅር ለብሔረስብ የመልማት አቅም የሚያሳንስ አደረጃጀት ሲኖር አወቃቀር እንዲሰፋ እንዲሁም ጭቆና ሲኖር ከተደራጀበት ከክልሉ እስከመውጣት በግልጽ ሕገ መንግሥቱ ደንግጓል፡፡ የክልሉ ሕገ መንግስት አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 2 እንደሚደነግገው የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ አስተዳደር መብት ጥያቄ ማንሳት መብት እንደሆነ ምላሹም በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚሰጥ ደንግጓል፡፡
ይህ መብት በምንም መልኩ ገደብ አልተጣለበትም፡፡ ከዚህም በላይ ይኸው የደቡብ ክልል መንግሥት የክልሉ የበላይ ህግ እንደመሆኑ መጠን ማንኛውም ህግ ልማዳዊ አሰራር መንግስታዊ አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ህገ መንግስቱ ጋር የሚፃረር ሆኖ ሲገኝ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ከመግለጹም ባሻገር ማንም ሰው የመንግስት አካላት የፖሊቲካ ድርጅቶችና ባለስልጣኖቻቸው ህገ መንግስቱን የማክበርና ተገዥ የመሆን ኃላፊነትና ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡
በደቡብ ክልል መሪ ፖሊቲካ ድርጅት የሆነው ደኢህዴን የአሁኑ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚ/ር እና በተለያየ የፌደራል መዋቅር ውስጥ በሚኒስተርነትና በከፍተኛ አመራሪነት ያሉ የደቡብ ክልል ተወላጅ ባለስልጣናት ከዳግም ተሃድሶ ጀምሮ በክልሉ ውስጥ ያሉ የደቡብ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የክልል፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ አስተዳደርና የማንነት ጥያቄ ማንሳት የክልሉን አንድነት መበታተን /መተርተር/ ነው የሚል ፖሊቲካዊ ውሳኔ በመወሰኑ ይኸው ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ደኢህዴንና ድርጅቱን የሚመራው የደቡብ ክልል መንግስት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በመሠረቱ የደኢህዴን በሕገ መንግስቱ የተሰጠውን የአደረጃጀትና የማንነት ጥያቄ መተርተር ነው በሚል ሰበብ የሰጠው ፖሊታካዊ ውሳኔ ሕገ መንግስታዊ ነው አይደለም? በዚህ ሕገ ወጥ ውሳኔ በብሔረሰቦች ላይ የደረሰው ኢ ሰብዓዊ ጭፍጨፋ፣ ንብረት ማውደም ወዘተ ተጠያቂ ማን ይሁን? እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ባጭር ባጭሩ በመመልከት የክልል አፌናና ልምዱ በጠ/ሚ/ር እየተመራች ያለችውን ኢትዮጵያን እያተራመሰ ለመንግስት መቀጠል ስጋት እየሆነ መምጣቱን እንመለከታለን፡፡
ከዚህ በላይ ስለ ክልሉ ህገ መንግሥት አንቀጽ 59 /2/ ድንጋጌ ስናወሳ የክልሉ ብሔር በሔረሰቦች ም/ቤት የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎችን በህገ መንግስት መሰረት ተቀብሎ ውሳኔ እንደሚሰጥ ሥልጣን ሰጥቷል፡፡ ድንጋጌው ህገ መንግስታዊ እንደመሆኑ መጠን በክልሉ ህገ መንግስት እንቀጽ 9/2፣3/ መሰረት የመንግስት አካል የፖሊቲካ ድርጅቶች ማህበራት ሁሉ፣ አክብሮት ሊሰጡና ሊጠብቁት እንደሚገባ ግዴታ ተጥሎባቸዋል ይላል፡፡
በመሆኑም በብሔረሰቦች የሚቀርቡ የማንነት፣ የአሰተዳደር አወቃቀር ጥያቄ በማንኛውም መስፈርት ህገ ወጥ የሚሆንበት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ባለመኖሩ ይህን ህገ መንግስታዊ ጥያቄ እንዳይነሳ የሚከለክል የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ውሳኔ ህገ ወጥ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በህገ ወጥ ውሳኔ መነሻ በዜጎች፣ በንብረት ላይ ለደረሱ ጉዳዮች ተጠያቂው ድርጅቱና የድርጅቱን ህገ ወጥ ውሳኔ የሚያስፈጽመው የደቡብ ክልል መንግስት አካላት ብቻ ይሆናሉ፡፡
በክልሉ ውስጥ ይህን የፖሊቲካ ድርጅት ህገ ወጥ ውሳኔ ተከትሎ በገሃድ በብሔረሰቦች ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች በጥቂቱ ሲንመለከት፡-
1) አለ ብሔረሰብ ወረዳ የማንነት ይታወቂልኝ ጥያቄ አንስቶ ክልሉ በብሔረሰቡ ላይ ወታደር አዘምቶ የበርካታ ሲቪሎችና የፀጥታ ኃይላት ሕይወትና ንብረት ጠፍቷል፡፡
2) ከፋ ሸካ ዞን በነበረበት አደረጃጀቱን በመቃወም የተንቀሳቀሱ ዜጎች የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሸካ ዞን ውስጥ የሸኮ መዥንግር ብሔረሰብ ማንነት ይታወቂልኝ ጥያቄ ታፍኖ ቀርቷል፡፡
3) በጉራጌ ዞን ውስጥ ስልጤ የማንነት ጥያቄ መልስ ያገኘ ቢሆንም የወለኔ ብሔረሰብ ጥያቄ ደም አፋስሶ በብሔረሰቡ ስብዕና ላይ ጉዳት አድርሶ እስከ ዛሬ 15 ዓመት ድረስ መልስ አላገኘም፡፡
4) የጎፋ ብሔረሰብ አደረጃጀት ጥያቄ የዜጎች ሕይወት የጠፋበትና በህብረተሰቡ ላይ ሥነ ልቦናዊ ተጽኖ አድርሷል፡፡ እስከ ዛሬ 15 ዓመት በላይ ምላሽ አላገኘም
5) በጋሞ ጎፋ ዞን ውስጥ የቁጫ ብሔረሰብ ማንነት ጥያቄ የሰው ሕይወትና ንብረት አጥፍቶ በርካታ ምሁራን ወህኒ ቤት ወርደዋል፤ በብሔረሰቡ ላይ ሥነ ልቦናዊ ጉዳት አድርሷል፤ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ምላሽ አልተገኘለትም፡፡
6) በደቡብ ኦሞ ዞን በኤርቦሬና በሐመር መካከል አሁን ያለው ግጭት መነሻ ኤርቦሬ ብሔረሰብ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ጥያቄ የበርካታ ሰው ሕይወትና ንብረት በማጥፋት ላይ ይገኛል፡፡
7) ሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ አንስቶ በርካታ የሰው ሕይወት ጠፍቶበታል አሁንም ብቅ ጥልቅ የማለት አዝማሚያ ይታያልበወጋጎዳ ዞን ሥር የተሰበሰበ የወላይታ፣ ጋሞ ጎፋ፣ ዳውሮ፣ የባስከቶና የኮንታ ሕዝቦች ከዞኑ ለመውጣት ባደረጉት ትግል በርካታ የሰውና የንብረት ውድመት አስከትሎ መልስ አግኝቷል፡፡
9) የኮንሶ ሕዝብ በሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን በግዴታ ያለ ሕዝቡ ፍላጎት እንዲደራጅ በመደረጉ ሕዝቡ አሁን ከዞኑ ወጥቶ አሁን ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ እና ህገ መንግስት በሚፈቅደው መሰረት ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት በዞን መዋቅር እንድደራጅ ሕጋዊ የአስራር ሥርዓት በተከተለ መልኩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ሆኖም በሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን ከመሰረቱት ከልዩ ወረዳ ወደ ወረዳ ዝቅ ብሎ በዞኑ ሥር በግዴታ እንድኖር የተደረገው የኮንሶ ብሔረሰብ ሕዝብ በዞን ተደራጅቶ ራሴን በራስ ችዬ ላስተዳድር ብሎ በብሔረሰቡ ም/ቤትና ሕዝብ ውሳኔ በህጋዊ መንገድ ያቀረበው ጥያቄ በደኢህዴን ህገ ወጥ ውሳኔ ጥያቄው መተርተር በመሆኑ መቆም አለበት በሚል በብሔረሰቡ ሰላማዊ ትግል ውሳነውን አልቀበልም በማለት በጠንካራ ሕዝባዊ መሰረት የታጀበ ትግል እየገፋ ያለው ማዕበል በፌዴራል መከላኪያ ሠራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልሉ ሚሊሻ ኃይል ከፍተኛና ዘግናኝ የሰው ሕይወት ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት አስከትሏል፡፡ በብሔረሰቡ ላይ የሞራልና ሥነ ልቦና ጉዳት አድርሶ ቀጥሎ ዛሬ ላይ ብሔረሰቡ ከክልሉ ጋር ላለመቀጠል ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል የደኢህዴን ውሳኔ ህገ ወጥ የሚያደርገው የክልሉን አንድነት ሊያጠናክር የሚችለው በህገ መንግስት ለብሔሮች ለብሔረሰቦች የተሰጠውን መብት በማክበርና በመፈጸም ተግባራዊ ማድረግ እንጂ መብቶችን በማፈን ብሔረሰቦች ከክልሉ ጋር የመኖር ዋስትናን አደጋ ውስጥ በማስገባት መበታተንን የሚያፋጥን ይሆናል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በብሔረሰቦች ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ ህገ ወጥ ነው ተብሎ በመፈረጅ በርካታ ብሔሮች ብሔረሰቦች የመብት ጥያቄ እንዳያነሱ በመታፈናቸው እንጂ ህገ መንግስቱ ቢከበር በደቡብ ክልል በርካታ ጥያቄዎች እንደሚነሱ ይታመናል፡፡ እንግዲህ የክልሉ ደኢህዴን ኢ ህገ መንግስታዊ በሆነ ውሳኔ በዜጎች ሕይወትና በንብረት ላይ ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ አደጋ ሲያስከትል ሕገ መንግስቱን ረግጧል፡፡ ከመብት ረጋጮች መካከል ድርጅቱንና መንግስትን በመምራት ይህ ህገ ወጥ ውሳኔ እንድወስንና አፈና እንድፈፀም በማዘዝ ሲሳተፉ ከነበሩት የዛሬ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ጠ/ሚ/ርና ሌሎች በፌዴራል ያሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሆኑት የደቡብ ክልል ተወላጆች ናቸው፡፡
እነዚህ የመንግስት አካላት የአገርቱን ቁልፍ የፖሊቲካና ወታደራዊ መዋቅሮችን የሚያዙ ስለሆነ በደቡብ ክልል የብሔረሰቦችን መብት ጥያቄ አፈና ደርሶበት ዜጎች እንዲጨፈጨፉ፣ ንብረት እንዲወድም የጅምላ እስራት የማድረግ ልምዳቸውን በማስፋት ከክልሉ ውጪ የሚነሱ የብሔረሰቦች መብት ጥያቄ ልክ እንደ ደቡብ ክልል ሁሉ ጥያቄዎች በጊዜው መልስ እንዳያገኙ በማፈን የመልካም አስተዳደር እጦት ጫና እንድኖር ግጭቶች ተፈጥረው በእጃቸው ይዘው በሚመሩት ፀጥታ ኃይል ለጭፍጨፋ በመላክ ሥነ ልቦናዊና ሰብዓዊ ጉዳት በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንድደርስ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ አካላት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም የሚያስቡ ቢሆን ኖሮ በክልላቸው ለበርካታ ዓመታት ሳይመለስ የቀረው የማንነትና መዋቅር ጥያቄዎችን መመለስ ጊዜ የሚወሰድ ባለመሆኑ ለአስርት ዓመታት ባላቆዩት ነበር፡፡ በዚህ ስሜት የሌሎች ብሔረሰቦች ጥያቄዎች ወደ ግጭት ተቀይሮ ደም ባላፈሰሰ ነበር፡፡
ደም ፈስሶ ንብረት ወድሞ ማየት የአመራሮች ዝንባሌና ልምድም ባይሆን ኖሮ ለቅማንት፣ ለወልቃይት፣ ለኮንሶና ለኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልሱ ወታደራዊ ምላሽ ባልሆነ ነበር፡፡ ስለዚህ በኢህአዴግ እህት ድርጅቶች መካከል ሊኖር የሚገባው ትግል ዝምታ ተሰብሮ የብሔረሰቦች መብቶች የአንድ ክልል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የመሰረቱት የሁሉም የብሔሮች ብሔረሰቦች የጋራ አንድነት ጉዳይ ስለሆነ በአንድ የአስተዳደር ክልል ውስጥ መጠቃለል ብሔሮች ብሔረሰቦች በሕገ መንግስት የተጎናጸፉትን መብቶች እንድታፈን ለሚያስተዳደር ክልል እና የብሔረሰቦችን አፈና በሚያስፈጽሙ ባለሥልጣን እናውቃለን ለሚሉት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ የብሔረሰቦች አፈና ኢትዮጵያን እንደአገር ለማስቀጠል አደጋና ከፍተኛ ትግል የሚጠይቅ በመሆኑ ብሔረሰቦችን በሚያፍኑ ክልሎችና አመራሮችን በተጀመረው ጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ በማስገባት ትግል እንድደረግባቸው ብሔረሰቦች ለሚይጠቁት ጥያቄ አስቸኳይ መፍትሔ በመስጠት ኢትዮጵያን እንድታደጓት ሲጠይቅ ከኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች የወጣችሁ ወታደር የሕዝብ ልጆች የኃይል እርምጃ በማያስወስድ ተራ ጥያቄዎች ውስጥ በሕገ ወጥ ትዕዛዝ በመግባት ከሕይወትና ከንብረት ውድመት ታቅባችሁ ለኢትዮጵያን ሕገ መንግስት ማበብ በብሔረሰቦች ጎን በመቆም ሕገ ወጥ አስተሳሰብ ያላቸውን አመራሮችን እንዲትታገሉና ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ እንድታወርዷቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠይቃል፡፡
የብሔረሰቦችን መብት ማስከበር የሁሉም ኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶች ትግል ሊሆን ይገባል!!!