ከጎንደርና ባህር ዳር የህዝባዊ እምቢተኝነት የተሠጠ መግለጫ!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እንደሚታወቀው አምባገነኑን ዘረኛ የህወሀት ገዥ ቡድን ከአገራችን ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማሥወገድ ህዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠሉ ይታወቃል፡፡ስለሆነም የፊታችን ማክሠኞ የሚከበረውን የመስቀል በአል ዘረኛው የህወሀት ቡድን የተለያዪ አገራትን ጋዜጠኞች ወደ አማራ ክልል በማስገባ ከተወሠኑ የአሸባሪ ቡድኖች አቀንቃኝ በስተቀር ህዝብ ከመንግሥት ጎን ነው በማለት ዶኪመንታሪ ፊልሞችን ለመሥራት የተዘጋጀ ሥለሆነ በተለይ በክልላችን ዋና ዋና ከተሞች ማለትም በባህር ዳር፥ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍኖተ ሠላም፣ በደብረ ታቦርና በደሴ ከተሞች የመስቀል በዓል በአደባባይ ስለማይከበር ህዝቡ ዝግጅት በማድረግ በየቤተክርስቲያኑ እንዲዬደርግ የትግል ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ በሠሜንጎንደርና ደ/ጎንደር ጳጳስ አቡነ ኤልሳ መሪነት የተደረገውን የስብሰባ ቃለ ጉባኤ አያይዘን ልከናል፡፡

በጐንደር የመስቀል በዓልን አከባበር በተመለከተ የተነሳው ውዝግብና የመጨረሻ ውሳኔው የ2009 ዓ.ም. የመስቀል በዓልን አከባበር በተመለከተ በዛሬው ዕለት መስከረም 13 ቀን 2009 ዓ.ም ረፋድ ላይ የሰሜን እና ደቡብ ጐንደር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ፣ በጐንደር ከተማ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች እና አገልጋዮች ያካተተ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ጠርተው ነበር። በስብሰባው ላይም በዚህ ዓመት የመስቀል በዓል በጐንደር ከተማ በአደባባይ እንደማይከበር ተሰብሳቢዎች ወስነው ተለያይተዋል። ዝርዝሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ስብሰባውን የጠሩት የዞኑ ቤተክነት ስራ አስኪያጅ አቶ ከለመወርቅ አሻግሬ ሲሆኑ ስብሰባው እንዲጠራ ያዘዙት ደግሞ የሰሜን ጎንደር ዞን እና
የደቡብ ጎንደር ጳጳስ የሆኑት አቡነ ኤልሳ ናቸው ፡፡ በስብሰባው መድረክ ላይ የተቀመጡት አቡነ ኤልሳ ፣ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ቀለም
ወርቅ አሻግሬ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ፀሀፊው አቶ ቀለም ወርቅ አለሙ ናቸው ፡፡
በስብሰባው የተገኙት:-
– የሁሉም አድባራት አስተዳዳሪዎች
– የሁሉም አድባራት ወንጌል ሰባኪያን
– የሁሉም አድባራት መርጌታዎችና
– የከተማዋ ታዋቂ ግለሰቦች ናቸው
በአጠቃላይ የስብሰባው አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በሙሉ የሞላ ሲሆን የስብሰባው አጀንዳ ፡- የመስቀል በዓልን አከባበር በተመለከተ መከበር
አለበት ወይስ የለበትም? እንዴትስ እናድርግ በሚል ነው?ሁሉም ተሰባሳቢዎች በከፍተኛ ደረጃ ሀሳ ለመስጠት እጃቸውን ያወጡ ሲሆን አንድ
ተሰብሳቢ ይህን የተሰበሰብንበትን አዳራሽ ፣ ቤተክርስቲያናትን ሌሎችንም ህንጻዎች የሚሰሩ ወጣቶች በበዓላት ወቅት ምንጣፉን እያነጠፉ
በራሳቸው ወጭ ሰረገላ አሰርተው በአሉን በአል የሚያደርጉትን ወጣቶች እየታሰሩ ፣ እየተገደሉ ፣ አየታፈኑ ፣ የት እነዳሉ እነኳን በማናውቅበት ሁኔታ በዓል እናክብር ብላችሁ መጥራታችሁ ያሳዝናልም ያሳፍራልም ብለው ሲናገሩ ተሰብሳቢው በሙሉ በጭብጨባ የተቀበላቸው ሲሆን ስለዚህ በምንም ተአምር ሊከበር አይገባም ብለው ሲጨርሱ ፡፡ ሌላኛው ተናጋሪ ተጨማሪ ሀሳብ የሰጡ ሲሆን ለተነሱት ነጥቦች ሊቀሊቃውንት እዝራ ሃዲስ ተነስተው ቀደም ሲል መከበር አለበት ብየ ተናግሬ ነበር አሁን ደግሞ ስብሰባውን የጠራነው መስከረም 7 ቀን ሶስት የመከላከያ ጄኔራሎች ፣ ብፁአባታችንን አቡነ ኤልሳን እንዲሁም ስራ አስኪያጁን አቶ ቀለምወርቅ አሻግሬንና ሌሎችንም ጠርተው በምንም አይነት ይህን
የመስቀል በዓል ሊከበር ይገባል በዓሉን አናከብርም የምትሉ ከሆነ እርምጃ እንወስዳለን በማለት የዛቻ እና ማስፈራሪያ ንግግሮች ሲያደርጉ
ዋሉ::
መጀመሪያ ላይ አታክብሩ ሲሉ የነበሩት እነዚሁ ጀነራሎች ሃሳባቸውን ቀይረው አሁን ደግሞ አክብሩ ማለታቸው ከጀርባው ሴራ አለው:: እንደዚህ ዜና ዘጋቢ ገለጻ “በአሉን እናከብራለን ነገር ግን ይህን በዓል በዋናነት የሚከበረው የሚያደምቀው ወጣቱ ነው በመሆኑም ወጣቱን ፍቱልን መከላከያም ከከተማው ይውጣልን እና እናከብራለን አልናቸው:: እነሱም ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በስልክ ተዎያይተው ከዚያም ሰዎችን አንፈታም እነዚህ የታሰሩት በህግ ይጠየቃሉ በማለት መልስ ሰጡን” እኛም ሲጨንቀን እናንተን ሰብስበን ምን እናድርግ ብለን ነው የጠራናችሁ አሉ? ስራ አስኪያጁም አቡነ ኤልሳ ሊቀሊቃውንት እዝራ ያሉት ትክክል ነው ለዚህ ነው የጠራናችሁ አሉ::

ከዚያም ከተሰብሰሰቢዎች አንዱ ጄኔራሎቹ እናንተን ጠርተው ከማናገር እኛን ለምን ጠርተው አያናግሩም:: ስለእኛ የመስቀል በአል እነሱ ምን
አገባቸው? የሚል ንግግር ሲመጣ ሁሉም በጭብጨባ ተቀብለውታል:: ከዚያም ሊቀሊቃውንት እዝራ ተሰብሳቢው ሁሉ ያለው ትክክል ነው:: እኔም መንግስት የሚሰማ መስሎኝ የታሰሩትን የሚፈታ መስሎኝ ነው በአሉን እናክብር ያልኩት አሁን ግን ሳየው ጎንደር የምትተዳደረው በወታደር ነው:: ሁኔታው የሚያሳዝንና ፀሎት የሚያስፈልገው ነው ብለው ይህ የመስቀል በአል በአደባባይ ሊከበር አይገባም ሲሉ በሙሉ ተሰብሳቢው ከወንበር በመነሳት በጭብጨባ ደግፏቸዋል:: ከዚያም ሰብሳቢዎቹ ሌላ የተለየ ሃሳብ ካለ እናክብር የሚል ካለ ብለው ጠየቁ ምንም
እናክብር የሚል ሰው ጠፋ:: ከዚህ በኋላ እንዴት እናክበረው ታዲያ የሚል ሀሳብ ከሰብሳቢዎቹ ተነሳ:: ተሰብሳቢዎቹም ሁላችንም በየደብራችን /በየቤተክርስቲያናችን/ እናክብር በማለት በጭብጨባ በሙሉ ድምፅ መስከረም 17 ቀን መስቀል በዓል በአደባባይ እንደማይከበር ተወስኗል፡፡ የመንግስት አካላት ግን በግልፅ ቤተክነት ጦርነት አውጃለች ማለት ነው ብለው ተናግረዋል ፡፡
ከጎንደርና ባህር ዳር የህዝባዊ እምቢተኝነት የተሠጠ መግለጫ
Source – Amhara Force / FB