ጠያቂ የተከለከለችው አስቴር ስዩም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አርማጭሆ ተወልዳ ያደገችው አስቴር ስዩም ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ከዓመት በፊት ማስተርሷን በማዕረግ አግኝታለች፡፡ብአዴን/ኢህአዴግ ካልሆነች በተመረቀችበት ሞያ ስራ ማግኘት የማይታሰብ መሆኑ ቢነገራትም ሰዎች ባላቸው ብቃት ተወዳድረው ስራ የሚያገኙበት ዕድልን የሚፈጥር ስርዓት እንዲገነባ ለማገዝ የቀድሞውን አንድነት ፓርቲ በመቀላቀል በአርማጭሆ ወገኖቿን ስታደራጅ መቆየቷ በስርዓቱ ሰዎች ጥርስ ውስጥ አስገብቷታል፡፡
አስቴር በሚደርስባት ጫና የተነሳእና አዛውንት እናቷን ለመደገፍ በማሰብ ከአንድ ዓመት ሶስት ወራት በፊት ወደአዲስ አበባ ትመጣለች፡፡ነገር ግን በአዲስ አበባ የተቀበሏት የማዕከላዊ ቅጥረኞች ነበሩ፡፡በማዕከላዊ ቆይታዋ በቤተሰብ እንዳትጎበኝ በማድረግ ጠንካራ መንፈሷን ለመስበር ብዙ ግፍ ፈጽመውባታል፡


አሁን አስቴር ለእስር ከተዳረገች አንድ ዓመት ከሶስት ወራት ያህል ተቆጥሯል፡፡ከማዕከላዊ ወደ ቃሊቲ ቢያሸጋግሯትም የቃሊቲው መንግስት ከጠያቂዎች ጋር እንዳትገናኝ አድርጓታል፡፡


የአንዲት ህጻን እናት የሆነችው አስቴር ልጇን ይንከባከቡላት የነበሩት ወላጅ እናትዋ በዕድሜ መግፋትና ጤና ማጣት ጋር ተያይዞ ህመምተኛ መሆናቸው ስጋት ፈጥሯል፡፡አስቴር ብቻዋን እንዳልሆነችና ጀግኖቹን የማይዘነጋ ህዝብ(ወገን)አጠገቧ እንደሚገኝ ለማሳየት ይህ የጎ ፈንድ የትብብር ማሳያ አካውንት ተከፍቷል፡፡ እናም ለአስቴር አለን እንበላት፡፡