ጥቃት በሰማያዊ ላይ – የወያኔ ምርጫ ቦርድ ህግን እየጣሰ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሰማያዊ ፓርቲ አገር ዉስጥ አሉ ከሚባሉ ደርጅቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በርካታ የድርጅቱ አባላት የታሰሩና መከራን የተቀበሉ ሲሆን ብዙዎችም ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።

የሐሳብ ልዩነቶች የማይንጸባረቅባቸው ድርጅቶች አምባገነን ድርጅቶች ብቻ ናቸው። አንድ ለዲሞክራሲ እታገላለሁ የሚል ድርጅት፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ሕገ ደንብ ያለው፣ በውስጡ የተለያዩ የሐሳብ ፍጭቶች፣ ልዩነቶችን ማስተናገሩ የግድ ነው። ከዚህም የተነሳ በሰማያዊ ፓርቲ ዉስጥ በሊቀመንመበሩና በሌሎች አመራር አባላት መካከል ልዩነቶች ተፌጥረው የነበረ ቢሆንም፣ አመራር አባላቱ ያሉ ልዩነቶችን በዉይይት ለመፍታትና ጠቅላላ ጉባዬ ተጠርቶ በድርጅቱ ደንብ መሰረት ዉሳኔዎችን እንዲተላለፉ መስማማታቸው ይታወቃል።

በዚህ መሰረት፣ ደንቡን ተከትሎ ጠቅላላ ጉብዬ የመጥራት መብት ካላቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነውና ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉብዬ የሆነው የኦዲት ኮሚሽኑ ለቅዳሜ መስከረም 14 ቀን ጠቅላላ ጉብዬ ጠርቶ ነበር። በሕጉ መሰረት ፓርቲዎች ጠቃላል ጉብዬ ሲጠሩ ምርጫ ቦርድ መገኘት ስላለበት፣ የኦዲት ኮሚሽኑ ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ በማስገባት ታዝቢ እንዲመጣ ጠይቆ፣ ጉብዬዉን ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ፣ ምርጫ ቦርድ ከሕግ ዉጭ ጠቅላላ ጉቡዬ መራዘም አለበት የሚል ምላሽ በመስጠት የፓርቲው ጠቃላል ጉብዬ እንዳይደረግ መሰናክል አቅርቧል።

የሰማያዊ ፓረቲ በዚህ ጠቅላላ ጉብዬው ወደ ኋላ ለጎተቱት ችግሮች እልባት ሰጥቶበት፣ ጠንካራ ሆኖ ይወጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ሆኖም ፓርቲው በጉብዬ፣ በዉስጣዊ አሰራር ችግሮቻቸውን ፈተው፣ ጠንካራ ሆነው እንዲወጡ የማይፈልገው ወያኔ፣ ልክ በአንድነት ፓርቲ ላዩ እንዳደረገው፣ ሰማያዊ ፓርቲ ላይ እየዶለተ ነው።

ከዚህ በታች የምርጫ ቦርድ ለሰማያዊ ፓርቲ የጻፈው ሕግ ወጥ ደብዳቤና የሰማያዊ ፓርቲ የኦዲት ኮሚሽንም የመለሰው መልስ እንደሚከተለው ተያይዟል።

የሕወሃት ባለስልጣናት በየሜዲያው እየቀረቡ “ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መቅረብ አለባቸው፣ ተቃዉሞዎች በሰላማዊ መንገድ መደረግ አለባቸው ..” እያሉ በአንድ በኩል ቢናገሩም፣ በሌላ በኩል ግን እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ባሉ ደርጅቲችና አባላቶቻቸው ላይ በዚህ መልክ የሚያደረጉት ጫና፣ ሰላማዊ ታጋዮች እንደ ጠላት የሚያዩ መሆናቸው አመላካች ነው። እድነ ሰማያዊ ፓርቲ ያሉ ድርጅቶች በነጻነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸው፣ ዜጎንች ከሰላሙ መንገድ ዉጭ ያሉ የመታገያ መንገዶችን እንዲከተሉ የሚገፋፋቸውም መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት በተቻለ መጠን ህዝብን እና አገርን በማስቀደም፣ ያሉ ልዩነቶች በደርጅቱ ደንብ መሰረት እንዲፈታ ቁርጠኝነት በማሳየት፣ ሰማያዊ ለመጉዳት ሰበብ ለሚፈለገው የወያኔው ቡድን መሳሪያ እንዳያቀበሉ፣ እንደ ወንድማማቾች ቁጭ ብለው እንዲነጋገሩና ችግሮቻቸው እንዲፈቱ፣ መፍታት ካልቻሉ ጠቅላላ ጉብዬው ለወሰነው ተገዢ እንዲሆኑ እንመክራለን።