ማዕከላዊ በእስር ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ቸኮል ለጥቅምት 10 ተቀጠረ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ስንታየሁ ቸኮል ለጥቅምት 10 ተቀጠረ

በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) በእስር ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ቸኮል ለሁለተኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት።

ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ መስከረም 12 2009 ዓ.ም በአራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም ብሎ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆበታል። ፍ/ቤቱ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮውን በመፍቀድ ተለዋጭ ቀጠሮ ለጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም ሰጥቷል።

ስንታየሁ ቸኮል፣ የታሰረበት ክፍል ውስጥ እንዲፀዳዳ እየተደረገ እንዳለ ለፍ/ቤቱ አቤቱታውን ማሰማቱን ለማወቅ ተችሏል።

ስንታየሁ ቸኮል ከነሐሴ 14 ቀን 2008 ዓ ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።