የስራ ማቆም አድማዉን ተቀላቅለናል ። ከወረታ የህዝባዊ እምቢተኛ አስተባባሪ ኮሚቴ የተላከ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከወረታ የህዝባዊ እምቢተኛ አስተባባሪ ኮሚቴ የተላከ

እንደሚታወቀዉ ባህርዳር፣ ጎንደር የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸዉ ይታወቃል።ከባህርዳር በ 55 ኪ/ሜትር እርቀት የምትገኘው ወረታ ከተማ ከ11/01እስከ13/01/2009 የሚቆይ የስራ ማቆም አድማዉን ተቀላቅለዋል።

ሆኖም ግን ዛሬ ወታደሮች የቻሉትን በሀይል ሲያስከፍቱ በአብዛኛው እንዲታሸጉ ሆነዋል በነገው እለት ማንኛዉም የንግድ ድርጅት እና ተሽከርካሪ አገልግሎቱን እንዳይሰጡ ።

በተጨማሪ የተወሰኑ ባጃጅ እና ሚኒባስ ሲንቀሳቀሱ ስላየን ሰሌዳ ቁጥራቸውን ይዘናል አድማውን የማይቀላቀሉ ከሆኑ ከባድ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እና የታሸጉ የንግድ ድርጅቶች እራሱ መንግስት ከአድማው በሁአላ የማይከፍት ከሆነ አድማው የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን።