“ለወገን ጥሪ የወገን ምላሽ” በሚል መሪ ቃል ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ተካሄደ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በወያኔ ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርገውን ጭፍጨፋ በመቃወምና አገር ውስጥ በተጠናከረ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ላለው የነጻነትና የፍትህ ትግል አጋርነት ለመግለጽ ታላቅ ትዕይንተ ህዝብ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያን ዘር፣ ሐይማኖት፣ ጾታ፣እድሜና በሌሎችም ምክንያቶች ሳይለያዩ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነው “ወያኔን ከጫንካችን ላይ ውረድ፣ ወገኖቻችን አትጨፍጭፍ፣ የህዝቡ ጥያቄ ትክክለኛና አግባነት ያለው ነው” የሚሉና በርካታ መፈክሮችን በመያዝ ልዩ የሆነ ፍቅርና መግባባት የታየበት ብዙ ሽህ ህዝብ የተቀላቀለው ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ መልክ ሁልቆ መሳፍርት የሌለው ኢትዮጵያዊ ከተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶችን እንዲሁም ከካናዳና አውሮፓ ጭምር በመሰባሰብ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ተቃውሞውን ካሰማ ወደ አሜሪካ ምክር ቤት ተሟል። VIDEO ↓
https://www.youtube.com/watch?v=sI7PDB8VgMc