ሃብታሙ አያሌው በቶሎ ሕክምና እንዲያገኝ ይደረግ – #ግርማ_ካሳ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወንድማችን ሃብታሙ አያሌው አሁንም በሕመምና በስቃይ ላይ ነው የሚገኘው። አረመኔዉ የሕወሃት አገዛዝ ሕክምና እንዳያገኝ ከልክሎት በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ ድኖ መንቀሳቀስ የሚችል ወጣት አሁንም በአልጋ ላይ ነው። ብዙ ጊዜ ደም እየፈሰሰው ሆስፒታል እየገባ ደም ይሰጠዋል። በጣም ተጎሳግሏል።
የሃብታሙን ጉዳይ የያዘው ፍርድ ቤት ነው ይባላል እንጂ የአገር ደህንነት እና የጸረ-ሽብር ግብረ ሃይል የሚባለው አሸባሪ ቡድን ነው። እነ ሶሞራ እነ ጌታቸው አሰፋ ያሉበት። የሐኪሞች ቦርድ ሃብታሙ ውጭ ሄዶ መታከም እንዳለበት የሚገልጽ ደብዳቤ ቢጽፍም፣ ይህ አሽባሪ ቡድን ግን በሃብታሙ ላይ የሞት ፍርድ ፍርዶበታል።
ኢትዮጵያዉይን በያለንበት ቦታ ለዚህ ወንድማችን እንጸልይ።እግዚአብሄር ፈዉሱን እንዲያዝለት። እነርሱማ አሁን ጉልበተኞች ናቸው። ቀን ይመጣል። በቅርብ። ታሪክ የሚቀየርበት። ያኔ በሃብታሙ ላይም ሆነ በሌሎች ላይ ላደረጉት ግፍ ሂሳብ ያወራርዳሉ። ከፍርድ ቤት ሰዎች ጀመሮ እስከነሶሞራ ድረስ ያሉ።
ከዚህ በታች የምታይዋቸው የአንጋፋው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት፣ የቀድሞ የሕወሃት አመራር የነበረችውና አሁን በአረና/መድረክ ዉስጥ ሕወሃትን እየታገለች ያለች አንጋፋ ታጋይ አረጋች እንዲሁም የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪ የሆነው ኡስታዝ አቡበከር ናቸው።