የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ህዝብ በ2008 የተገደሉትን፣ ለእስር፣ ለወከባ፣ ለድብደባ፣ ለቃጠሎ የተዳረጉ ልጆቹን ያስባል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አከባበር ሥነ ስርዓት

*******************************

 

ዘንድሮ የኦሮሞ ህዝብ የ2016/2009 የኢሬቻ በዓል አከባበር ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በአባ ገዳዎች መሪነት በነፃነት በሆራ አርሰዲ ያከብራል። ከአባ ገዳዎች መዋቅር ውጭ የየትኛው የኦህዴድ/ኢህአዴግ ካድሬዎች ጋጋታ በአካባቢው እንዲሰማ አይፈቀድም።

 

የአባ ገዳዎች አባ ዱላ ኦቦ ድንቁ ደያሳ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ በራሱ መዋቅር ሰርጎ ገቦችን ይቆጣጠራል። ስመ ጥር የሆኑ አለም አቀፍ ሚድያዎች በቦታው በመገኛት የኦሮሞን ህዝብ ሰላም ወዳድነትና ስነ ስርዓት አክባሪነት የሚያረጋግጡበት ቀን ይሆናል። የኦሮሞ ህዝብ ሴት ወንድ ወጣት ሽማግሌ ሳይል ባህላዊ ልብሱን በመልበስ ወደ ሆራ አርሰዲ ይተማል።

 

ጩሀትና ግርግር አይኖርም። የኦሮሞ ህዝብ በተረጋጋ መንፈስ ፈጣሪውን ዋቃን ያመሰግናል። በ2008 በመንግስት ታጣቂዎች የተገደሉትን፣ ለእስር፣ ለወከባ፣ ለድብደባ፣ ለቃጠሎ የተዳረጉ ልጆቹን ያስባል።

 

በዚህ አጋጣሚ የኦሮሞ ህዝብ ታላቅ ህዝብ መሆኑንና ራሱን በራሱ መምራት እንደሚችል ለዓለም ህዝብ ያስመሰክራል።