ህወሐት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የነበረው ሰብሰባ እርቃኑ የወጣበት፣ ብዙ የፎረሸበትና ብዙ የከሰረበት ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Image result for mekelle university teachers meetingኢህአዴግ ለ8 ቀናት በጠራው የመምህራን ስልጠና እንኳን ሊያተርፍ ብዙ ብዙ እየከሰረ እንደሆነ ግልፅ እየሆነ ነው፡፡ለምሳሌ የህ.ወ.ሐ.ት ምሽግ ተብላ በምትታሰበው መቐለ፣ ሊያውም ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ በመሰለ የህ.ወ.ሐ.ት የፖሊት ቢሮና የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የነበረው ሰብሰባ ኢህአዴግ እርቃኑ የወጣበትና፣ ብዙ የፎረሸበትና፣ ብዙ የከሰረበት ነው፤

መጀመርያ ንጉሰ ገብረ በሚባሉት ከአራት ዐመት በፊት ከህ.ወ.ሐ.ት ማዕከላይ ኮሚቴነት ወርደው የነበሩ ሰው በመሩት ሌላኛው ሰብሰባ ከተነሳው ብዙ ቁምነገር አንዱ:-አንድ ትንታግ ተነሳ፤ “የደባርቅ ሰው ነኝ፤ የአኒማል ሳይንስ ባለሙያ ነኝ፡፡ ባለፈው እናቴ ዘንድ ቆይቼ ወደዚህ ልመለስ ስል እናቴ ፈርታ እንዳትሄድ አለችኝ፡፡ እኔ ግን የትግራይ ሕዝብ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፤ ጨዋና ርሕሩሕ፣ በዘር፣ በሐይማኖት፣ በምን ብትለው በስሜት ተነሳስቶ የማይሆን ድርጊት የማይፈፅም እጅግ ጨዋ ሕዝብ ነው፡፡ ስለዚህም እሄዳለሁ ብየ ወዲህ መጣሑ፡፡ ሁለት ዝሆኖች ሲጣሉ ሳሩ ነው የሚጎዳው ይባላል፡፡ ህ.ወ.ሐ.ትና ብአዴን ሁለት የዝርፊያ ቡድች በምታደርጉት የስልጣን ሽኩቻ ለዘመናት በፍቅር የኖረ የትግራይና የአማራ ሕዝብ ለእሳት መማገድ ታስባላችሁ፤ አባይ ወልዱና ገዱ አንዳርጋቸው ስላልተዋደዱ ተብሎ ሕዝብ እንዲጠፋፋ መማገድ፤ ይህ ታሪክ ይቅር ማይለው ወንጀል ነው፡፡ ደግሞ የአማራ ሕዝብን ‘ትምክሕተኛ’፤ ትግራይን ሕዝብ ‘ጠባብ’ ማለት አምጥታችኃል፡፡ እኔ ግን ትምክሕቱም ጠባብነቱም ያለው ኢህአዴግ ውስጥ እንጂ በሕዝቡ ላይ አይደለም ነው የምለው፡፡ ለምሳሌ ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት የአካዳሚክ ማዕከላት መሆን ሲገባቸው፣ እውቀት ያለው ማንም ቢሆን ሊመራቸው ሲገባ በየክልሉ ያሉ ኒቨርሲቲዎች የክልሉ ተወላጆች ብቻ እንዲያስተዳድሯቸው መምርያ አውጥታችኃል፡፡ ከዚህ በላይ ምን ጠባብነት አለ ደግሞ ከኛ በላይ ለዚች ሐገር የሚያስብ፣ የሚሆን የለም ትላላችሁ፤ ትምክሕትስ ይኼ!”

ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ ወደ መሩት እንመለስ፤

ሰብሰባው ሐሙስ ጧት ሲጀምር ዶ/ር አዲስ አለም ብቻውን የተለመደውን ኢህአዴጋዊ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሲያወራ አረፈደ፡፡
ሐሙስ ከሰዐትም እንዲሁ ፕሮፖጋንዳውን ጀመረና እንዲህ አለ ጥያቄ ካላችሁ ለየዲፓርትመንት ሐላፊዎቻችሁ ስጡና እነሱ ጨምቀው ይሰጡኛል፡፡ እዚህ ጥያቄ አልቀበልም፤ የወጣው መርሐ ግብር እንደዚያ ነው፡፡
ሁሉም ሰው ደስተኛ አልነበረም፤ በቡድን በቡድን ተሁኖም ጥያቄዎች ተሰበሰቡ፡፡
ዐርብ ጧት “ትላንት ከናንተ ለተሰበሰቡ ጥያቄዎች መልስ” ብለው ፈፅሞ ያልተጠየቁ፣ ያልተባሉ እርባናቢስ ጉዳዮችን አንስተው የተለመደውን ህ.ወ.ሐ.ታዊ ፕሮፖጋንዳ ቀደዱ፡፡
ተሰብሳቢው እጅግ ተቆጣ፡፡ ዶ/ር ገብረየሱስ የሚባሉ ትንታግ ምሁር አንደኛ ጥያቄዎቻችን እየተመለሱ አይደለም፤ የጠየቅናችሁ መሰረታዊ ጥያቄዎች ትታችሁ እንቶ ፈንቶ እያወራችሁ ነው፡፡ እዚህ ብዙ ሐሳብ መስጠት የሚችል ምሁር አለ፡፡ ለምንድነው ነገሩን ቀልድ የምታደርጉት፡፡ 25 ዐመት ሙሉ ዋሻችሁን፤ የኛ ዕድሜም ጨረሳችሁት፤ በሐገርና በሕዝብ ቀለዳችሁ፤ ሐገርም ይኸው ከፍተኛ አደጋ ላ ወድቃለች፡፡፡፡ እሺ የኛ ዕድሜስ ሄዷል፤ ብዙ ዕድል ከፊታቸው ያሉ ብዙ ወጣት ምሁራን ግን እዚህ አሉ፡፡ እዚህ ብዙ ጠቃሚ ሐሳቦች ሊሰጥ የሚችል በጣም ብዙ ምሁር አለ፡፡ ጥያቄዎቻችንን በስነ-ስርዐቱ በማስታወሻ ያዙና በመንግስት ደረጃ ከፍተኛ ውይይት ይደረግባቸው፡፡ አለበለዚያ ለ25 አመታት በቲቪውን በሬድዮውም የሰማናቸው ተራ ውሸቶች እዚህ ቁጭ ብለን የምንሰማበት ምክንያት የለም፡፡
አደራሹ ጭብጨባና ሁካታ ሆነ፤ ደ/ር አዲስአለም ወደ ስድብና ወደ ማስፈራራት ገባ፤ ነገር ተበላሸ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላም ሰብሰባው ተበተነ፡፡ ከሰዐት በኃላም የነበረው የተሰብሳቢው መንፈስ ቁጣ ብስጭት የሚስተዋልበት ነበር፡፡ ዶ/ር አዲስአለም ባሌማም እንዲሁ ሰውን ትንሽ አንጓጠውና አስፈራርተው ለጥቂት ደቂቃዎች የሆነ የሆነ ብለው ሰብሰባውን በትነው ሄዱ፡፡