በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ በዛሬው ዕለት ተጠርቶ የነበረው ”ለቅሷዊ ጸሎት” በምዕመናን ድርቅ ተመታ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
- የምዕመናን ቁጥር ከተጠበቀው እጅግ አነስተኛ ነበር
- ለምዕመናን ቁጥር መመናመን ዋናው ምክንያት ከሳምንት በፊት ደብሩን ረግጠው በነበሩት አባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) ምንያት ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው
- መምህር ዘበነ በቅርቡ አገራችን ውስጥ በወያኔ እየተጨፈጨፉ ለሚገኙት ወገኖቻችን የሰጠውን ወያኔን የሚደግፍ እንዲሁም ከወንጌል የወጣ ምላሽ በርካታ ምዕመናንን ማስቆጣቱና ማሳዘኑ እየተነገረ ነው
- ቆሞስ አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ፣ መምህር አሸናፊ ዱጋ፣ መምህር ዶ/ር ቀሲስ አንዱዓለም፣ ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ተፈራና ሌሎችም የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ወያኔን የሚያወግዝና የሚኮንን ጠንካራና ትክክለኛ ትምህርት መስጠታቸው መምህር ዘበነን ብቻ በወያኔ ደጋፊነት ተነጥሎ አንዲታይና እንዲጋለጥ አድርጎታል የሚል አስተያየትም እየተሰጠ ነው
- ጸጥታ ለማስጠበቅና ለትራፊክ ተጠርተው የነበሩት ፖሊሶች የመጣው ህዝብ ቁጥር አነሰተኛ በመሆኑ ለምን እንደተጠሩ ሳይገረሙ አልቀረም ተብሏል
መምህር ዘበነ ለማ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እጅግ አፋኝ፣ ጨፍጫፊና ኢሰብዓዊ የወያኔ አገዛ ላይ ምንም ዓይነት ትችት፣ተግሳጽ፣ ተቃውሞና ውግዘት ማድረግ አያስፈልግም “የክርስቲያኖች ተግባር መጸለይ ብቻ ነው” በማለት በሚሰጠው የተዛባ ስብከት ምክንያት ብዙ ተቃውሞ ሲሰነዘርበት እንደቆየ ይታወቃል። ቁጥራቸው በቀላሉ የማይገመት ምዕመናንን እሱ አሜሪካ ከመምጣቱ በፊት እጅግ ጠንካራ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ የሱን ስብከት በመስማት ለአገራቸው ተግባራዊ አስተዋፅኦ እንዳያደርጉና በወያኔ ላይ ጠንካራ አቋም እንዳይወዱ አሽመድምዷቸዋል እየተባለ በስፋት ይነገራል። በተለይም በተለያየ ጊዜ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በወያኔ ላይ የተደረጉትን የተቃውሞ ሰልፎች “ክርስቲያኖች ለዓለማዊ መሪዎች አቤቱታ አናቀርብም እኛ ወደ ሰማይ ብቻ ነው የምንጮኽው” እያለ አወደ ምህረት ላይ ቆም በማጥላላቱ በርካታ ምዕመናንና ካህናት ሲቃወሙት ኖረዋል።
ከአንድ ዓመት በፊት በሊቢያ በሰማዕትነት ላለፉት ኢትዮጵያውያን ዋሽንግተን ውስጥ ተካሂዶ በነበረው የጸሎት ዝግጅት ላይ ወያኔን የሚያወግዙ ጠንካራ የሃይማኖት አባቶች በአቡነ መቃሪዎጽስ መሪነት ባካሄዱት ዝግጅት ላይ “ከመንግሥት ያጋጨኛል” በማለት ሌላ የግሉ ዝግጅት ማድረጉ አይዘነጋም። መምህር ዘበነ ለማ እንደለመደው በዛሬውም ዕለት ቴምፕል ሂልስ፣ ሜሪላንድ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ የጠራው የለቅሶና የጸሎት ዝግጅት በቅርቡ አገራችን ውስጥ በወያኔ ለተጨፈጨፉት ወገኖች እንጸልያለን የሚል ስም የተሰጠው ሲሆን ወያኔን በማያስቀይም ሁኔታ እጅግ በተለሳለሰ ሁኔታ የተካሄደ እንደነበር ተገልጾልናል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ንጹሃን ዜጎችን እንደ ከብት አያረደ ባለበት ጊዜ መፍትሄው ነፍሰ ገዳዩ ከድርጊቱ እንዲታቀብ ማስገደድ መሆኑና ህዝብ የህይወት ዋጋ እየከፈለባቸው ላሉት ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ መስጠት መሆኑ እየታወቀና መፍትሄውም በሰው እጅ (በወያኔ አጅ) የሚገኝን ነገር “መቅሰፍት”፣ “መዓት” ወይም “የፈጣሪ ቁጣ” አንደወረደ አስመስሎ ሁኔታውን አጣሞና ኣወላግዶ ለምዕመናን የተሳሳተና የተንሸዋረረ ትምህርት እየሰጠ ነው። መምህር ዘበነ ይህንን በማድረግ ህዝብ ያነሳቸው የህልውና ጥያቄዎች እንዳይመለሱ እንዲሁም በማለቅ ላይ ያለው ህዝብ ዝም ብሎ እንዲታረድና ለወያኔ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ በተዘዋዋሪ መንገድ እያመቻቸ መሆኑን መረዳት አያዳግትም።
በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን ይመጣሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ካህናትና ምዕመናን ብቻ መገኘታቸው መምህር ዘበነ ለማ በወቅታዊው የአገራችን ሁኔታ ላይ ከህዝብ ጎን ከመቆም ይልቅ ከወያኔ ጎን በመቆሙ ምክንያት ነው በማለት የቤተክርስቲያን ጉዳይን እግር በእግር የሚከታተሉ ምዕመናን እየተናገሩ ነው። በዛሬው የመምህር ዘበነ ዝግጅት ላይ ይመጣሉ ተብለው ለነበሩ ምዕመናን የትራፊክ መጨናነቅን ለማስወገድ ከቤተክርስቲያኑ ሂሳብ ወጭ በማድረግ ተቀጥረው የነበሩ ፖሊሶች የመጣው ተሳታፊ እጅግ አነስተኛ ስለነበር ምንም ሳይደክሙ በዕረፍት ነው ያሳለፉት የሚል አስተያየትም ተሰጥቷል። (እንደውም አንዳንድ ቀልደኞች ፖሊሶቹ እጅግ ብዙ ወንጀል በሚፈጸምበት የፕሪንስ ጆርጅ ወረዳ ውስጥ ሲደክሙ የሚውሉ ስለሆነ የተጨማሪ ሰዓት ክፍያ ተደርጎላቸው አንድ ቀን አርፈው መዋላቸው መልካም ስራ ነው የሚሉም ተደምጠዋል። የተደረገው የጸሎትና የሐዘን መግለጫ ሁኔታም በመምህር ዘበነ ለማ የተመራ ሲሆን አካሄዱ ያልተለመደና አንዳንዶችን ግራ ያጋቡ እንግዳ ሁኔታዎችም የታዩበት ነበር ።
ምንም እንኳ እንደ መምህር ዘበነ ለማ ያሉት ሀቁን ጨፍልቀው ከነፈሰ ገዳዮች ጋር አብረው ቢሰለፉም ማህጸኗ የማይነጥፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያፈራቻቸው በርካታ እወነተኛ መምህራን አሏት። ከነዚህም መካካል መምህር ዶ/ር ቀሲስ አንዱዓለም “አባቶችህ የሰሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍርስ” እንዲሁም ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ተፈራ “የደሙ ድምፅ” በሚል ርዕስ ወቅታዊው የአገራችንን ጉዳይ አስመልክተው የሰጧቸውን ትምህርቶች አቅርበንላችኋል።
መምህር ዶ/ር ቀሲስ አንዱዓለም “አባቶችህ የሰሩትን የቀደመውን የድንበር ምልክት አታፍርስ”
ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ተፈራ “የደሙ ድምፅ”