የኢሕአዴግ የተሀድሶ ተምሳሌት የኢንደስትሪ ሚንስትር አህመድ አብተው የሙስናው ንገሥ !!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አህመድ አብተው የተባለው በሙስና የበሰበሰ ሰው ወሎ ዩንቨርሲቲ ስለመታደስ ሲያወራ ምሽት ዜና ላይ ሰማሁት። አቶ አህመድ የዐማራ ክልል የገጠር መንገዶች ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የተገኘባት የሙስና ወንጀል እስካሁን ይገርመኛል።

የዐማራ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲተሮችን (በ2004 ዓ.ም ይመስለኛል) የኦዲት ባለሙያዎችን ወደ ገጠር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት ላከ። ወያኔ ተፈጻሚ ያልሆን ሁሉንም የገጠር ቀበሌ በመንገድ ማገናኘት በሚል እርዳታና ብድር ከዓለም ባንክ የሰበሰበበት ወቅትም ነበር።
የሆነው ሆኖ የኦዲት ባለሙያዎቹ የክልሉ ገጠር መንገድ የተከራያቸው እና ውድ የኪራይ ዋጋ የሚወጣባቸው ሁለት የመንገድ መደምደሚያ ቡልዶዘር መኪናዎች ይገኛሉ፤ ኦዶተሮቹ ፋይሉን ሲመረምሩ የአቶ አህመድ አብተው ሆነው ተገኙ።
ጉዱ በዚህ ቢያበቃ ጥሩ ነበር፤ ለመሥሪያ ቤቱ በእርዳታ ከመጡት ቡልዶዘሮች ሁለቱ ይጠፋሉ። ፋይል ሲገላበጥ ሊብሬያቸው በአቶ አህመድ ስም መግባታቸውን አሳየ። አቶ አህመድ በስሙ ያደረገውን የሕዝብ ሀብት መልሶ በውድ ዋጋ ኃላፊ ሆኖ በሚሰራበት መሥሪያ ቤት እያከራየ ቸክ እራሱ እየጻፈ ይበላል።
ኦዲተሮች ሪፓርት አደረጉ። የክልሉ ምክር ቤት ጉድ አለ። ከዚያም በአስተዳደር ውሳኔ ይሰጠው ተብሎ “አፉ” ተባለ። በኋላም አቶ ኃይለማርያም የኢንደስትሪ ሚንስትር አድርጎ አሳደገው። እዚያ ሂዶ ምን ፋብሪካ በስሙ እንዳደረገ እግዜር ይወቅ።
ይህ ግለሰብ የሀይቅ ሀይቅን አደጋ ላይ የሚጥል ፕሮጀክትም ተፈጻሚ በማድረግ ይታወቃል።

የኢሕአዴግ የተሀድሶ ተምሳሌት አህመድ አብተው!!Muluken Tesfaw