በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ቤታቸው በክረምት የፈረሰባቸው ኣባወራዎች ኮሚቴ 14 ኣባላት ማእከላዊ አየተሰቃዩ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ቤታቸው በክረምት የፈረሰባቸው ኣባወራዎች ኮሚቴ 14 ኣባላት ማእከላዊ አየተሰቃዩ ነው።

በክረምቱ ወራት መኖሪያ ቤታቸው በሕወሓት ኣገዛዝ የፈረሰባቸው ኣባወራዎች ከነቤተሰቦቻቸው እየተንገላቱ መኖሪያ ማጣታቸውን ኣምርረው በመናገር ላይ ሲሆኑ ጉዳያቸውን እንዲያስፈጽሙላቸው የወከሏቸው ኮሚቴዎች 14 ኣባላት በማእከላዊ የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በየቀኑ በክፍለከተማው በር ላይ ደጅ የሚጸኑትና ሰሚ ያጡት ኣባወራዎቹ ቤታቸው ከፈረሰ በኋላ ሰሚ ኣጥተው ሲንገላቱ የቆዩ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ኣጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ወያኔ መሬት እሰጣቹሃለሁ በማለት ኣዲስ ኮሚቴ ኣዋቅሩ ቢልም ኣሁንም ኣዲስ ኮሚቴዎችን በድብቅ በማስፈራራት ሕዝቡን ጸጥ ለማሰኘት በመስራት ላይ ይገኛል፥ ኣሁንም በድጋሚ ሕዝቡን ውክልና ስጡ ኮሚቴ ተዋቅሯል በማለት ለማደነጋገርና የሕዝብን ጥያቄ ለመድፈን ወያኔ ተግቶ እየሰራ አው ሲሉ ቤታቸው የፈረሰባቸው ኣባወራዎች በምሬት ይናገራሉ። ምንሊክ ሳልሳዊ