መምህራን ከዝምታ ባለፈ በአንዳንድ አደራሾች ቁጣቸውን መግለጽ ጀምረዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
መምህራን ከዝምታ ባለፈ በአንዳንድ አደራሾች ቁጣቸውን መግለጽ ጀምረዋል።
#Ethiopia #EthiopianTeachers #EthiopiaProtests #MinilikSalsawi #EPRDF
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ክልሎችን ሳይጀምር በኣዲስ አበባ ብቻ እየተደረገ ያለው የመምህራን ስልጠና ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ በዝምታ ተቃውሞ የታጀበ ቢሆንም በዛሬ እለት በኣንዳንድ ኣከባቢዎች በስልጠናው መድረክ መሪዎች ግፊት ዝምታዎች የተሰበሩ ሲሆን መምሕራን ቁጣቸውን ሲገልጹ ካድሬዎች በውጪ ሃይሎች ባሏቸው ኤርትራና ግብጽ ትከሻ ላይ ታዝለው ውለዋል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ገረጅ በቦሌ በመካኒሳ ኣራትኪሎ ስድስት ኪሎ ኣራዳ እና የመሳሰሉት ኣከባቢዎች በተካሄደው የመምህራን ስብሰባ ላይ የተገኙ ምንጮች እንዳሉት ከመድረኩ በጎንደርና ባህርዳር ላይ ስለተፈጠረው የትምህክተኞችን ሴራ አስረዱ በተባለ ሰዓት የስልጠናው ተሳታፊዎቹ ያቀረቡትን ሀሳብ ትምህክተኛውና አሸባሪው መንግስት እንደሆነ በድፍረት ተናግረዋል፣ ይህ የተነሳ አመፅ ይበርድ ዘንድ መፍትሄም አስቀምጠዋል፣ ከመፍትሄዎቹ ውስጥ መንግስት ይውረድ፣ኢኮኖሚው በጥቂት ባለ ሀብቶች ብቻ አይወሰን ህዝብን ያማከለ ይሁን በማለት ተናግረዋል።ይህንን ንጝግር ሊናገሩ የቻሉት ካልተናገራችሁ በማለት አስገድደው ነው።እናም ተናጋሪ መምህራኖች በመናገራቸው ጉዳት ይደርስባቸዋለን ብለን ስጋቱ አለን። ብለዋል መምህራኖች። የግድ ተናገሩ ብለው ካስናገሩ በሗላ ለእስር የሚዳርጓቸው ከሆነ ለህዝብ ለማሳወቅ ይረዳ ዘንድ የመምህራኑ ስም ዝርዝር በመረጃው ጸሃፊ እጅ ይገኛል ።እንዲሁም በማህበራዊ ድህረገጽ ዙሪያ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ የመድረኩ ስልጣና መሪዎች የተባሉ በማንሳት ለማጣጣል ቢሞክሩም ሰሚ ጆሮ ኣላገኙም ሲሉ በስልጠናው ተካፋይ የሆኑ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
በግድ እንዲናገሩ የተገፉ መምህራን በተለያ በኦሮሚያና በኣማራ ክልል ስለተፈጸሙ ጭፍጨፋዎች በቁጭት ሲናገሩ ተደምጠዋል፤ የወያኔ መንግስት ያበቃለትና ሕዝቡም ከመንግስት የተሻለ ንቃተ ሕሊና ላይ ስለሚገኝ ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ መምህራን ኣበክረው ሲናገሩ ተሰምቷል። ተናገሩ ብላቹ ነገር እንዳታመጡ በኋላ የናንተ ነገር መጨበጫ የለውም ሲሉ መምህራኑ የመድረኩን መሪዎች ተችተዋል።በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት መግስታት ጋር ስናነጻጽረው እንደ ኢሕ ኣዴግ ሕዝብን የጨፈጨፈ ኣምባገነን የለም ያሉ ኣንድ መምህር ኣሁን ተናገሩ ኣናስርም ትላላቹ እውነት ስለተናገሩ ብቻ የታሰሩ እነእስክንድር ነጋና ሌሎች ጋዝዔጠኞች እና ጦማርያን በቂ ምሳሌ ናቸው እንዚህ የመናገር ነጻነት የመጻፍ ነጻነት ኣለ ተብለው የታሰሩ መፈታት ኣለባቸው ዛሬ እኛ ተናግረን በምህረት ተፈቱ ተብሎ ፕሮፓጋንዳ በተሰራባቸው የተፈቱ የሕሊና እስረኞች ምትክ ላለመተካታችን ምን ዋስትና ኣለን ሲሉ ጠይቀዋል።
የፌዴራል ስርዓቱን ለከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ እና ብሄሮችን ለማጋጨት የስልጣን እድሜን ለማስረዘም ተጠቅማቹበታል ሲሉ የተቹ አንድ መምህር ኢሕ አደግ ከመጣ በሁኣላ ህዝቡ ለረሃብ፣ ለስደት፣ ለሞት ፣ ለተለያዩ ችጊሮች ተ ጋልጧል በማለት በዝርዝር ኣስቀምጠዋል፤የመድረኩ የስልጣና መሪዎች የተባሉ ካድሬዎች ፊታቸው ላይ በተኮሳተር ሙድ ቁጣ የሚነበብ ሲሆን መልሱን ሰኞ ጠብቁ በማለት ለመምህራኑ ጥያቄ እና ኣስተያየት መልስ መስጠት ኣለመቻላቸው ዝምታው ከመምህሩ ወደ መድረኩ ተቀይሮ እንደነበር ተሳታፊዎች ጠቁመዋል። #ምንሊክሳልሳዊ
