የመምህራን የተማሪዎችን የወላጆችን ስልጠና በኣዲስ መስመር ኣዲስ የትግል ስልት የሚከፈትበት መንገድ መጥረጊያ በማድረግ የወያኔን ውድቀት በጋራ እናፋጥን።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የመምህራን የተማሪዎችን የወላጆችን ስልጠና በኣዲስ መስመር ኣዲስ የትግል ስልት የሚከፈትበት መንገድ መጥረጊያ በማድረግ የወያኔን ውድቀት በጋራ እናፋጥን።
Minilik Salsawi – በወያኔ የሚሰጡ ስልጣናዎችን እንደከዚህ ቀደሞ በማክሸፍ በኣዲስ መስመር ኣዲስ የትግል ስልት የሚከፈትበት መንገድ መጥረጊያ በማድረግ የወያኔን ውድቀት በጋራ እናፋጥን ለስርነቀል የስርዓት ለውጥ ስኬት ተማሪዎችና መምህራን ታሪካዊ የዜግነት ግዴታ ኣለባቹህ።ከመምህራን ኣከባቢ የሚሰሙ ጉምጉምታዎች ኣሉ ነበሩ ይህንን ጉምጉምታ ኣፋቸውን ይይዝልኝ ይሆናል በሚል የወያኔ ኣገዛዝ በደሞዝ ጭማሪ ተስፋ ኣጡዞ መምህራኑ ግን በሃምሌ የተገባው ቃል ወዴት ኣለ ሲሉ ይጠይቃሉ፤ የኦሮሞ ተማሪዎችን ንቅናቄ ተከትሎ የወያኔ ኣገዛዝ በውስጡ ሰርጾ ፍርሃትና ቁርጠት በለቀቀበት ጊዜ ከኣጣብቂኙ ለመውጣት ያልቧጠጠው ያልደሰኮረው የለም፤ከዚህ ጋርም በተያያዘ ቀጣዩ ጊዜያትን ከፍራቻው ለመላቀቅ የትምህርት ጊዜን በማቃጠል የልመናና የማስፈራሪያ ስልጣና ለመምህራን ለወላጆችና ለተማሪዎች በመስጠት ጉዞውን ጀምሯል።

መምህራንን እና ተማሪዎችን የዘላለም ባሪያ ኣድርጎ ነጻነት ኣልባ ኣድርጎ ለመግዛት የስልጣኑ ወንበር ተሸካሚ ለማድረግ ደፋ ቀና የሚለው ወያኔ በኦሮሚያ በኣማራና በደቡብ ኢትዮጵያ በኮንሶ ወዘተ ከፍተና የሆነ የዘር ማጽዳት በመፈጸም ላይ ይገኛል፥ ሕዝቡን መብታቸውን እንዳይጠይቁ በዲሞክራሲ ሽፋን በጥይት እየፈጀ የሚገኘው መፍጤ ኣልባ ኣገዛዝ በፈጣን መልኩ ከስልጣን እንዲወገድ የመምህራን እና የተማሪዎች ድርሻ የበለጠ መሆን ይገባዋል።
የሕዝብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማንነት በመዝረፍ ነጻነትንና መብትን በማሳጣት በጥቅም በተበተባቸው ካድሬዎቹ ተከቦ የመማርና የማስተማር ነጻነትን በመንፈግ የትምህርት የጥራት ደረጃ በማውረድ ትውልዱ ሞራለ ቢስ ያደረገው ኣገዛዝ በመምህራት ላይ በማሳበብ ወላጆችን በማጥላላት በትውልዱ ዙሪያ እየቀረጸ ያለው ራእይ ኣደገኛ በመሆኑ ልናከሽፈው ይገባል። መምህራንና ተማሪዎች በቀታይነት በሚካሄደው ትግል የራሳቸውን ድርሻ በማበርከት ዜጎችን ከግድያና ከእስር በመታደግ በኢትዮጵያ ስር ነቀል የሆነ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ሊሰሩ ይገባል።የታሪክ ኣሻራቸውንም ከኣምባገነን የነጻች ኢትዮጵያ ለመረከብ ለተዘጋጀው መጭው ትውልድ ላይ ሊያትሙ ይገባል።በየቦታው በወያኔ የሚሰጡ ስልጣናዎችን እንደከዚህ ቀደሞ በማክሸፍ በኣዲስ መስመር ኣዲስ የትግል ስልት የሚከፈትበት መንገድ መጥረጊያ በማድረግ የወያኔን ውድቀት በጋራ እናፋጥን ። #ምንሊክሳልሳዊ Minilik Salsawi – mereja.com