የጀግናው ደመቀ ዘውዱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለ5ኛ ጊዜ ወደ መስከረም 9/2009 ዓ.ም. አሸጋግሮታል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገኝው የወያኔ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ዛሬ የተሸጋገረውን የጀግናው ደመቀ ዘውዱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለአምስተኛ ጊዜ ወደ መስከረም ዘጠኝ ቀን 2009 ዓ.ም. አሸጋግሮታል።
በፍርድ ቤቱ ደጃፍ ከተሰበሰበው እልፍ የአማራ ወጣት በላይ የአማራ ደም ሊጠጣ ከተማዋን የወረራት የትግራይ ነፍሰ በላ ወታደር ይበልጥ ነበር። ሞት የማይፈራው አዲሱ የአማራ ትውልድ ግን እስከ አንፍጫው የታጠቀውን የትግራይ ጦር ከመጤፍ ሳይቆጥር የጀግናውን የፍርድ ቤት ውሎ በፍርድ ቤቱ ደጃፍ ቆሞ ይጠባበቅ ነበር።
አሁን ግን ጀግኖቹ የጎንደር ወጣቶች በሰላም ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። የአማራ ተጋድሎ በቆራጥ የአማራ ልጆች ትግል በድል ይደመደማል! achamleh Tamru