በኮንሶ ውጥረቱ አይሏል። የሚገደለው የሚታሰረውና የሚፈናቀለው ሕዝብ ቁጥር ጨምሯል። የምንሊክ ሳልሳዊ ዝርዝር ዘገባ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኮንሶ ውጥረቱ አይሏል። የሚገደለው የሚታሰረውና የሚፈናቀለው ሕዝብ ቁጥር ጨምሯል።
የምንሊክ ሳልሳዊ ዝርዝር ዘገባ #Ethiopia #KonsoProtests #EthiopiaProtests #SouthEthiopia

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኮንሶ የአከላለልና ማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ህዝባዊ ቁጣ ከተሻገረ ካለፉት ኣመታቶች ጀምሮ የሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ በሕዝቡ ላይ የከፋ ኣደጋ እና ሰቆቃ በመፈጸም በግዳያ በእስር በማሳደድ ሕዝቡን እያንገላታው ይገኛል።በዚህ ሰሞን በከፍተኛ ደረጃ በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ የሕወሓት ኣገዛዝ በዞኑ ባፈሰሰው የኣግዓዚ ሰራዊት እየተመራ የኮንሶን ሕዝብ በማፈናቀል በመግደል በመዝረፍ በማሰር ላይ ይገኛል።ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በተደጋጋሚ ለፌደራል መንግስት አመልክተን ነበር፤ እዚህ ያለው የክልሉ መንግስት ግን ምን ብሎን ነበር ‹‹እዚህ ያለነው እኛ እዛም (ፌደራል መንግስቱ ላይ) ያለው እኛ የትም ብትሄዱ መልስ አታገኙም›› ብለውናል”ሲሉ በምረት ይናገራሉ።
መስከረም 3/2009 የከልል ልዩ ኃይል ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ሆነዉ በኮንሶ አርሶአደር ላይ የከፈቱት የግድያና ቤቶችን የማቃጠል ዘመቻ ከመስከረም1/2009 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቀጥሏል፡፡ በዛሬዉ ቀን መከላከያ ሠራዊት ሕዝብ ላይ ጥይት እየተኮሰ አርሶአደሩ ከቀዬአቸው ስሸሹ የጉማይዴ ጥገኛ ከሥር ከሥር እየሮጠ የ80 አርሶአደሮች መኖሪያ ቤት መቃጠሉ እና የ5 አርሶ አደሮች ሕይወት አልፏል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊእነዚህ የሕወሓት ሀይላት ተቀናጅተዉ በሕዝቡ ላይ የከፈቱት ዘመቻ ከባድ መሣሪያን በመጠቀም አንድ ቤት ላይ በለቀቁት ትኩስ ደግሞ አንድ የ8 ወር ሕፃን ሕይወት አልፏል እናቱም በከባዱ ቆስላለች፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊረዳ የሚገባ ጉዳይ፦ ዛሬ ዛሬ ላይ የኮንሶ ተወላጅ 1- ሕይወቱ በየቀን በመከላከያ እየተጨፈጨፈ 2-መንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ለ7ወር ተከልክሎ 3- የድሀ ድሀ አርሶአደር እርዳታ ተከልክሎ 4-የአርሶ አደር ቤት በየቀን እየተቃጠለ ይህ ሁሉ ስሆን የኮንሶ ተወላጅና ወዳጆቹ የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸዉን የሚያስክድ ሰቆቃ እየደረሰበት ነዉ፡፡ የደቡብ ክልል ሙሉ ሀይሉን ሰብስቦ ሙሉ ክንዱን ዘርግቶ የኮንሶን ሕዝብ ከካርታ ላይ ለማጥፋት ካለፉት ኣመታቶች ጀምሮ ተንቀሳቅሷል በተግባር እያሣየ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያ በየቀን የንፁህ አርሶአደር ደም በጥይት በየማሣ እየፈሰሰ ይገኛል፡ምንሊክ ሳልሳዊ ስለ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ግድ ልላችሁ ይገባል፡ እንቅልፍ ልነሳችሁ ይገባል፡ በቻላችሁ አቅም ይህንን ምስክን ሕዝብ ልታግዙ ይገባል፥፥ በየአለም አቀፍ ሠልፎች እና ተቃዉሞዎች ላይ የኮንሶ አርሶ አደር ደም ሊታወስ ይገባል እላለሁ፡፡በሌላ በኩል ሠገን ዞን የበተኑ ጥገኛ አመራሮች እየታሰሩ መሆኑ የተነገረ ሲሆን አንዳንዶቹ በልዩ ሀይል ተደብድበዉ እግራቸዉ ተሰብሯል (ኩያዎ ዘመዱ፡ ኻማሌ ቀበሌ፡ ራሱን ዉሀ ጽ፨ቤት ላይ የሾመ)፣ ተደብድቦ የተጎዳ (ገዝሐኝ አይላዶ)፣ ሌሎች ኡርማሌ ኡጋንዴን ጨምሮ ከአሥር በላይ የሚሆኑት በከባድ ወታደራዊ ቁጥጥር በሠገን ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፡፡
በሰላማዊ መንገድ ጥያቄውን ያቀረበው የኮንሶ ሕዝብ ከሕወሓት ኣገዛዝ የተሰጠው መልስ ቢኖር የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ የኮንሶ ነዋሪዎችን ከስራ ገበታቸው ተባረዋል፣በወረዳው ላይ ያሉ ከ160 ፖሊሶች 152ቱን ትጥቅ አስፈትተው ከስራ አባረዋቸዋል ፣በዞን ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችም ከብዙ ጫና የተነሳ ከስራ ለቀዋል፣በክልሉ መንግስት ትዕዛዝ የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተዋል፣አስተማሪዎች(መምህራን) እና የመንግስት ሰራተኞች ባጠቃላይ የአራት ወር ደሞዝ አላገኙም፣ካሉት11የጤና ጣቢያዎች 11ም ተዘግተዋ::ጤና ጣቢያውም የሚያስጠብቁት በፖሊስ ነው፤ በዚህም ምክንያት እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ውስጥ አንድ ወላድ እናት ህክምና ባለማግኘቷ ህይወቷ አልፏል፣በምዕራባውያን ከድህነት ወለል በታች ላሉ ሰዎች እንዲሰጥ የሚላከው ገንዘብ (ሴፍትኔት) ከስድስት ወር በላይ አልተከፈላቸውም፡፡ የኮንሶ ሕዝብ ስቃይ ቀጥሏል በኮንሶ ውጥረቱ ኣይሏል፥፥የኮንሶ ሕዝብ የኢትዮጵያዊ ወገኖቹን ድጋፍ ይሻል። #ምንሊክሳልሳዊ