ችግሮችን ከልማቱ የመነጩ/ከውጭ ሃይላት የተቃጡ/በስልጣን ያለ አግባብ ከመጠቀም የወጡ እያሉ ማሳነስና ማድበስበስ መፍትሄ አይሆንም
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ችግሮችን ከልማቱ የመነጩ/ከውጭ ሃይላት የተቃጡ/በስልጣን ያለ አግባብ ከመጠቀም የወጡ እያሉ ማሳነስና ማድበስበስ መፍትሄ አይሆንም
ፓስተር እስጢፋኖስ ቱፋ
ስሜ ፓስተር እስጢፋኖስ ቱፋ ሲሆን ላለፉት 20 አመታት ሰዎችን የጽድቅ ኑሮ እንዲኖሩ -አምላካቸውን በመታዘዝ ለመንግስትና ለህዝብ መልካም ስራን እንዲሰሩ መልካም ዜጋን ለማነጽ ስሰራ ቆይቻለሁ. ለአገሬም ለእናንተ ለመሪዎቼም ብዙ ግዜ ጸልያለሁ.መንግስት ለሰራቸውን መልካም ስራዎች እውቅናም እሰጣለሁ.እኔም ሆንኩ ሌሎች የወንጌል አማኞች እንደዜጋ የአገራችን የህዝባችን ጉዳይ የማያገባን አይደለንም. የኦርቶዶክሳዊያን የሙስሊም የአማራ የኦሮሞ የሌላውም ወንድሞቻችን ህይወት ግድ ይለናል.ክቡር ጠ/ሚ ለቴክኖሎጂ ብዙ አሳይቶናል.በእርስዎ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከበስተጀርባዎ ባለ የአንደ ጎጠኛ ቡድን ግፊት በመተማ ተደፍተው የቀሩት ህጻናት -ሴቶች-ወጣቶች ባሌ ጎባ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ወታደርዎ የደፋው ወጣት -ባህር ዳር በስናይፐር ደሙ የፈሰሰው ወጣት ለገሃር ፖሊስ ጣቢያ እንደ እባብ የተቀጠቀጡት -መስቀል አደባባይ በፌደራል ከስክስ ጫማ ጥፊ መንጋጋቸው የተሰባበረው ቪዲዮ ተመልክተናል. በአደባባይ እንዲህ ከተደረገ በባንቢስ ኢ.ሲ.ኤ ገባ ብሎ -በጦር ሃይሎችና በሌሎች የደህንነትዎ ማሳቃያ ቢሮዎች ምድር ቤቶች የሚሰራው ግፍ ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት ከባድ አይደለም. ይህንን ግፍ ለመቀበል ባለመፈለግዎ ከጸሎትም ባለፈ አካፋን አካፋ ማለትና ለጥቅምዎ እርስዎንም መገሰጽም እንደሚገባ አምናለሁ. ማን ስለሆንክ ለሚለኝ የወንጌል አገልጋይ ስለሆንኩ እላለሁ. 2ሳሙ 12-9 ነብዩ ናታን ንጉስ ዳዊትን ንጹህ ሰው የሆነውን ኦሪዮንን ደም ስላፈሰሰ ገስጾታል አስጠንቅቆታልም. ዳዊት አንድ ነፍስ በማስገደሉ ከተገሰጸ እርስዎና የደህንነትና የመከላከያ ተቋሞ የብዙ ሽህ አላፈሰሱምን??? ኤሊያስም ንጉስ አክአብን አስጠንቅቆአል ገስጾአል. መጥምቁ የሐንስ በሁዋላ አንገቱን ቢያስቆርጠውም ንጉስ ሄሮድስን የወንድሙን ሚስት ማግባቱ ትክክል እንዳልሆነ ገስጾታል. እርሶ የማያውቁት የማሰቃያ ቢሮና የማሰቃየት ስልት ባይኖርም የወደዱትን ያድርጉ እንጂ የሚሰሩት ስራ ደም ማፍሰስና-ግፍ- መሆኑን በድፍረት እነግርዎታለሁ. ክቡር ጠ/ሚኒስትር እርስዎ ሲምቦል ሆነው የሚመሩት ግን መከላከያውን -ደህንነቱን -ኢኮኖሚውን -ሃይማኖቱን ሙሉ በሙሉ ሌላ ሃይል የተቆጣጠረው መንግስት በአለፉት 25 አመታት ህዝብ ደም ማስለቀሱ የታወቀ ነው. በተለይም በሚከተሉት አራት ጉዳዮች ዙሪያ በደልና ጥፋት ደርሶአል 1. ዲሞክራሲ እጦት – ጎልቶ የወጣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራርን – ስርአቱን የሚተች ጋዜጠኛና ብሎገርን… በጸረ- ሽብር/ጸረ ሙስና ህግ አጥምዶ መያዝ መብቱን የሚጠይቅ ዜጋን በማእከላዊና በደህንነት ቢሮዎች መደብደብ -ማሰቃየትና- መግደል -ህዝብ የሚያከብራቸውን አርቲስቶች በተቀነባበረና በሃሰተኛ ምስክሮች በተደገፈ ክስ ማሰርና ማሰቃየት/መደብደብ – 2. ኢኮኖሚያዊ ኢ -ፍትሃዊነት -አስቀድሞ የኢኮኖሚ የበላይነትን ለመያዝ በተነደፈ እቅድ የአምራች-የአስመጭና ላኪ -የአገልግሎት ሰጭ ተቁዋማትን ጥሬ እቃ አቅርቦትና የገበያ ድርሻ በጉልበትበመቆጣጠር ተፎካካሪን በተለያዩ ህጎች በመጥለፍ መጣልና ሞኖፖሊ መያዝ የስርአቱ አይነተኛ መገለጫ ነው. ያለቀረጥ ወይም በዝቅተኛ ቀረጥ እቃ በማስገባት ህጋዊውን ነጋዴ መጣል -የፋይናንስ ተቁዋማትን በመቆጣጠር የውጭ ምንዛሪን በማውጣት የመኪና -የኮንስትራክሽን ማሽኖችን -ኮምፑተር-መለዋወጫዎችን …ወዘተ ንግድ በብቸኝነት በመቆጣጠር ሌላውን ማዳከም -በአምራች/በሆቴሎች/በአስመጭና ላኪ …ወዘተ የሚሰማሩ ባለሃብቶችን ሸር ካላስገባችሁን አትነግዱም በማለት ሰርቶ እንዳይበላ ማድረግ-የከተማ ቦታዎችን የገጠር የእርሻ መሬቶችን በዘመድ አዝማድ በመቆጣጠርና ህንጻዎችንና ትልልቅ እርሻዎችን በመስራት ያለአግባብ መበልጸግ-ለስርአቱ ደጋፊ ኮንትራክተሮችና አገልግሎት ሰጭዎች የመንግስት ስራን ያለጨረታ ወይም በተጭበረበረ ጨረታ ኮንትራት መስጠት-ለስርአቱ ደጋፊ ኮንትራክተሮችና አገልግሎት ሰጭዎች የመንግስት ስራን ያለጨረታ ወይም በተጭበረበረ ጨረታ ኮንትራት መስጠት-የኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ ለስርአቱ ደጋፊዎች የተለየ እደላ -በመንግስትና ቀበሌ ቤቶች ላይ እነሱን መሰግሰግ- 3. አድልዎ – 99 ከመቶ የሆነው ከፍተኛ ወታደራዊና ደህንነት አዛዥነት ስልጣን ከህዝቡ 5ከመቶ በሆነ የአንድ ብሄር ሰዎች ብቻ መያዝና ሰራዊቱን ሞት ላለበት ግዳጅ ብቻ መፈለግ-የሲቪል መስሪያ ቤቶች የሃላፊነት ቦታዎች ታማኝ ናቸው በሚል እውቀት በሌላቸው በአንድ ብሄር በመያዛቸው ለሁዋላ ቀር አሰራር ለመጉላላት ለሃብት ብክነት መዳረግ -በስብሰባና በስልጠና ስም ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የአገሪቱን ገንዘብ ለፖለቲካ ትርፍ ለታማኞቻቸው በአበል ስም ማባከን- በያመቱ ብዙ ወጣቶች ተመርቀው እያለ ብዙ የስራ እድል ባለባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አየር መንገድ/ቴሌ/ገቢዎች/ጉምሩክ …ወዘተ የአንድ ብሄር ወጣቶች እየተመረጡ መቀጠር-ሌሎች በአገራቸውና በክልላቸው ሁለተኛ ዜጋ እንዲሆኑ ማሰብ. 4. የስልጣን ስግብግብነት -ስፖርቱን -ሃይማኖቱን -እድሩን …ወዘተ በሁሉ ላይ ባለስልጣን የመሆን የስልጣን ረሃብ ማለትም የኦርቶዶክስ ፓትሪያሪክነት በተጨማሪ ቤ/ክ ስር ያሉትን 17 መምሪያዎች በሙሉ በአንድ ብሄር አባላት መቆጣጠር -ሃፈ,ገረ ስብከቶችን -ደብራትን …ወዘተ መያዝ /የስፖርት ፌዴሬሽኖችን (ብስክሌት-ዋና-ኦሎምፒክ…)ወዘተ ያሉትን በስግብግብነት መቆጣጠር -በሌሎች ክልሎች ሳይቀር ስልጣን መያዝ…ወዘተ ክቡር ጠ/ሚ ችግሮችን ከልማቱ የመነጩ/ከውጭ ሃይላት የተቃጡ/በስልጣን ያለ አግባብ ከመጠቀም የወጡ እያሉ ማሳነስና ማድበስበስ መፍትሄ አይሆንም. ተቃዋሚን 24 ሰአት የሚሰልል እንቅስቃሴአቸውን የሚቆጣጠር የስለላ ተቋሞ የፍትህ እጦቱን -የኢኮኖሚ ኢ-ፍትህአዊነቱን አድልዎውን አያውቀውም -ያልታወቀ ሃብት የፈጠሩትን ባለህንጻ ጀነራሎቹዎን አልሰማሁም ቢሉኝ ቀልድ ይሆናል.ጉዳይ ለማስፈጸም ቀበሌ ሲሄድ መብራት የለም የሚለውን የአምስት ሽህ ብር ጀነሬተር መግዛት የማይችለውን ግን የኢህአዴግ ፖሊሲና ስትራቴጂ ስብሰባ 1000 ሰዎችን ሰብስቦ 70 ብር በነፍስ ወከፍ አበል ስለሚሰጠው ወረዳ አላውቅም አይበሉኝ….ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን መንግስትዎ ካወቀበት ይህ ለለውጥ መልካም አጋጣሚ ይጠቀምበት. እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ ፓስተር እስጢፋኖስ ቱፋ