የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ረቂቅ አቀረበ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
The #USA Congress is speaking out against tyranny in #Ethiopia.የዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ረቂቅ አቀረበ

የአፍሪቃ ጉዳዮች ንዑስ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ- መንበር ክሪስ ስሚት
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የተነጣጠረ ረቂቅ ውሳኔ በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ።
ዋሽንግተን —
በሪዮ ኦሎምፒክ ሁለት እጆቹን በማጣመር ተቃውሞ ያሳየው ኢትዮጵያዊ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከዩናይትድ ስቴትስ የምክርቤት አባል ክሪስ ስሚዝ ጋር በካፒቶልሂል ፊት ለፊት
የአፍሪቃ ጉዳዮች ንዑስ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ- መንበር ክሪስ ስሚት መሪነት የቀረበው ረቂቅ ሕግ በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች ላይ የሚወስሷቸው የኃይል እርምጃዎች እንዲቆሙ፤ ግድያዎቹ በዓለም አቀፍ ገለልተኛ ወገኖች ማጣራት እንዲደረግባቸውና እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ መሪዎችንና ጋዜጠኞችን በአስቸንኳይ መለቀቅ የሚጠይቅ ነው።