ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ለአዲስ ዓመት የአገራችንን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ውስጥ ወያኔ በሕዝብ ላይ ያደረገውን ጭፍጨፋ ማንም ክርስቲያን ነኝ የሚል በሙሉ ማውገዝ እንዳለበትና ከሚጨፈጨፈው ህዝብ ጎን መሰለፍ እንደሚገባውና እወነትን ብቻ መመስከር እንዳለበት ከመጽሃፍ ቅዱስ አስደግፈው ወቅታዊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።  በዚህም መሠረት መጥምቁ ዮሐንስ ለሞት ያበቃው በወቅቱ የነበረው ንጉስ ከህግ ውጭ የፈጸመውን ድርጊት በማውገዙና ይህም የህይወት ዋጋ እንዳስከፈለው በዝርዝር አሳይተዋል። ይህ ትምህርት በተለይ ጨፍጫፊዎችንና ግፈኞችን ማውገዝና መኮነን አይገባም እያሉ ለወንጀለኞች ሽፋን ለሚሰጡ አስመሳይና አወናባጅ ካህናትና መምህራን ነይ ባዮች ጥሩ ምላሽ አንደሚሰጥ ይታመናል።