ከቂሊንጦ ማረሚያ ወደ ዝዋይ እና ሸዋ ሮቢት የተወሰዱ እስረኞች ከፍተኛ እንግልት እና ስቃይ ላይ ናቸው
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በቃጠሎ ምክኛት ከቂሊንጦ ማረሚያ ወደ ዝዋይ እና ሸዋ ሮቢት የተወሰዱ እስረኞች ከፍተኛ እንግልት እና ስቃይ ላይ እንደሆኑ እና የቃጠሎ መንስኤም እናንተ ናችሁ እየተባሉ እንደሆኑ የታሳሪ ቤተሰቦች ገለፁ ።

ሪፖርተሮቻችን ያናገሯቸው የተለያዩ የታሰሪ እናቶች እንደገለፁት ከ250 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘን ልጆቻችንን እንዳናናግር ተደርገናል ይላሉ “በመጀመሪያ ቀናቶች አይተን ብቻ እንድንወጣ… የተደረገ ሲሆን ። አሁን ደግሞ ለሶስት ደቂቃ ያክል ብቻ “ሰላምታ ተለዋውጠን” እንድንወጣ ተደርገናል” ይላሉ ።
ወላጆች እንደገለፁት እስረኞቹ ከፍተኛ መጎሳቆል ላይ እንደሉ ከፊታቸው ማንበብ ቢቻልም መናገር የሚፈልጉትን እንዳይናገሩ በመደረጋቸው ያሉበትን የስቃይ ሁኔታ ከልጆቻቸው አንደበት እንዳይረዱ ተደርገዋል ።
በአሁን ሰዓት እስረኞቹ እየተጠበቁ ያሉት ከዚህ በፊት ባሉ የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ሳይሆን በአጋዚ ልዩ ሃይል መሆኑን የገለፁት ቤተሰቦቻቸው… <<እናንተ ነብሰ ገዳዮች ናቹ እናንተ ባነሳችሁት እሳት ነው ሰዎች የሞቱት ፣መቀጣት አለባቹ >> እየተባሉ እንደሚያሸማቅቋቸው እና ከፍተኛ ቅጣት በመቀጣት ላይ እንዳሉ የእስር ቤቱ የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል ።