በደም እየተጠመቁ አዲስ ዓመት አይጠባም! [በላይነህ አባተ]
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በላይነህ አባተ ([email protected])
በአዲስ ዓመት ልጃገረዶች በአደይ አበባ፣ በጠልስም፣ በመስቀል፣ በድሪ፣ በአንባርና በአልቦ ተውበው አበባየሁ ሆይን ይዘምሩ ነበር፡፡ እነዚህ ልጃገረዶች ዛሬ ክር አስረው፣ ፊታቸውን ልጠውና ራሳቸውን ተላጭተው ለታረዱት ወንድሞቻቸውና አባቶቻቸው ሚሾ ያወርዳሉ፡፡ ጎረምሶች በአዲስ ዓመት ችቧቸውን አብርተው “በቆላ በደጋ ያላችሁ …