ምንም አትችሉም ነው ስለዚህ ስልጣን ልቀቁ ነው አራት ነጥብ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የበሰበሰ እንዳያሸትና የከፋ በሽታ እንዳያስከትል ተጠራርጎ ይወገዳልና በቃን ብለናል፡፡ኣንዳንዶች የሽጝግር መንግስት ይቋቋም የጥምር መንግስት ይመስረት ወዘተ ይላሉ ይህ እኔ ኣይገባኝም እኔ የሚገባኝ ሕወሓት የሚባል ኣጭበርባሪ ማፊያ ደም መጣጭ ቡድን ከስልጣኑ ተነስቶ/ወርዶ በኢትዮጵያ ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ ሲደረግ ብቻናቻ ነው።። የሚገባው ይግባው የማይገባው ገደል ይግባ ኣሁንም ።። ወገኔ ክብሩ ተገፎ መብቱንና ነጻነቱን ኣጥቶ እስከመቼ ትግሉ ዘረኛና ከፋፋይ ጠባብ ትምክህተኛ የሆነውን ሕወሓትን ከስልጣን ኣውርዶ በኣዲስና በትኩስ ሃይል የተሞላ ሃገራዊ ሕብረት ያለው መንግስት ለማቋቋም ነው።

ሕወሓት ይሁን በስሯ በጥቅም ገዝታ የምታሽከረክራቸው ባለስልጣናቷ ከመግደል ከማሰር እና ከመዝረፍ ውጪ ሕዝብን ማስተዳደር ስላልቻላቹ ስልጣኑን ሕዝብን ለሚያስተዳድር ኣካል ልቀቁ ብትባሉ እምቢ ስላላቹ በሕዝብ ሃያልነት ኣንስተን እንፈጠፍጣቹሃለን እደግመዋለሁ ምንም አትችሉም ነው ስለዚህ ስልጣን ልቀቁ ነው አራት ነጥብ በአራቱም አቅጣጫ በምታየው ህዝባዊ እምቢተኝነት– ከፋፋይ ሴራችሁን ሰብረን በአንድነት በመቆማችን፣ ለኃይል አምልኮኣችሁ አለመስገዳችንንና ለመብታችን ለክብራችን ለነጻነታችን የቱንም መስዋዕትነት በመክፈል ማረጋገጣችን ፣ለዲሞክራሲና ሰላም ባሳየነው ቁርጠኝነት አረጋግጠናልና አዲስ መስራት እየቻልን እናንተ በየሰዓቱ ስናድስ አንኖርም፣ የበሰበሰ ደግሞ እንዳያሸትና የከፋ በሽታ እንዳያስከትል ተጠራርጎ ይወገዳልና በቃን ብለናል ፡፡