ስለቂሊንጦ ጥቂት መረጃዎች –
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ስለቂሊንጦ ጥቂት መረጃዎች
———– Elias Gebru Godana
የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊን አግኝቶ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ለማጠናከር እጅግ ከብዷል። ግን የሰማሁትን ጥቂት ነገር እንዲህ እናገራለሁ።
– ሁለት እስረኞች የአተት በሽታ እንደተገኘባቸውና ይህንንም ተከትሎ ከቤተሰብ (ከውጪ) የሚመጣ ምግብ ለእስረኞች እንዳይገባ መባሉንና ይህንንም ተከትሎ በእስር ቤቱ ሃላፊዎችና በተወሰኑ እስረኞች መካከል የሀሳብ ግጭት መፈጠሩን
– ተነሳ በተባለው ቃጠሎ በአንድ ክፍል ውስጥ እስረኞች (ቁጥራቸው እስካሁን ያልታወቀ) በጭስ ታፍነው እንደሞቱ
– በዕለቱ በተፈጠረው ችግር የሞቱ እስረኞች በጥቁር ላስቲክ ተጠቅልለው በመኪኖች እንደወጡ፤ የእነዚህ ቁጥርም 38 ገደማ እንደሚደርስ
-እነአቶ በቀለ ገርባ የነበሩበት ክፍል አለመቃጠሉን ነገር ግን ማን ይጎዳ ማን ተለይቶ አለመታወቁን ከምንጮች ሰምቻለሁ፤ ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ ባይቻልም።
ለእውነተኛ መረጃ ይህንን ያህል መዳከር ይሳዝናል -ጋዜጠኝነት አድካሚ ስራ መሆኑ ባይዘነጋም። ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት አካል በአግባቡ ቢኖር ኖሮ፤ የተፈጠረውን ሁነት በሙሉ ዘርዝሮ መግለጽ፣ በሰቀቀንና በጭንቀት ውስጥ ለሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች፣ ወገኖች፣ ወዳጆችና ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ በወቅቱ ዘርዝሮ በተናገረ ነበር። ዛሬም ድረስ የእስረኛ ቤተሰቦች በሀዘን ስቃይ ውስጥ ናቸው።
ትናንት ማታ የአንድ ተጠርጣሪ ፖለቲከኛ ሚስት በቪኦኤ ላይ ቀርበው “ቤተስቦቻችን ያሉበትን በግልጽ ንገሩን፤ ከሞቱም አስከሬናቸውን ስጡንና እርማችንን አውጥተን እንቅበራቸው!” ሲሉ ነበር – በሀዘን ተውጠው።
መራራውን እውነት ንገሩን!!