እጅግ ወቅታዊና አንገብጋቢ መልዕክት በመምህር አሸናፊ ዱጋ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
መምህር አሸናፊ ዱጋ በአገራችን ውስጥ በአሁኑ ወቅት በወያኔ አማካይነት በመድረስ ላይ ስላለው ጭፍጨፋና እንዲሁም በአጠቃላይ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ በጫነው “ከፋፍለህ ግዛ” ሥርዓትና በጎሳ ፖለቲካው ምክንያት አገሪቱ ውስጥ እየደረሱ ያሉትን የተወሳሰቡ ችግሮች ተንትነው ከነመፍትሄው አቀበውልናል። መምህር አሸናፊ የሐይማኖት አባቶች ሥራቸውን በመስራት ላይ እንዳልሆኑና አገሪቱ ለተዘፈቀችበት የመከራ አዘቅት የችግሩ እንጅ የመፍትሄው አካል አለመሆናቸውን አውግዘው ከአሁን በኋላ መሰራት ያለባቸውን ተግባሮች በዝርዝር አስቀምጠዋል። እኝህ መምህር እንዲህ አይነት ቆራጥነትንና ጽናትን የሚጠይቅ መልዕክት በማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ይህንን እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ሙሉውን ተከታተሉት።