­

ገንዘባቸውን ከባንክ ለማውጣት የሞከሩ ደምበኞች በፖሊስ ተደበደቡ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Run on Ethiopian banks following months of civil unrest in Oromia and Amara regions of Ethiopia

በበርካታ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች ገንዘብ የለም የተባሉ ደምበኞች “ያስቀመጥነውን ገንዘባችንን እንፈልገዋለን፣ ለልጆቻችን ትምህርት ቤት ወጪና ለአዲሱ ዓመት ያስፈልገናል፣ ገንዘባችን ካልተሰጠን አንሄድም” ስላሉ በፖሊስ ድብደባ ደርሶባቸዋል።

የባንኮች ቀውስ ወደ አዲስ አበባ እየተቃረበ ሲሆን፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ዋና ባንኮች ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ከወትሮ የበለጠ ገንዘባቸውን በቦርሳና ሻንጣዎች ስያወጡ ተስተውለዋል።

ቀድሞ ከብሄራዊ ባንክ መረጃ የሚደርሳቸው የህዋሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በገፍ እያሸሹ ነው። በነገው እለት እስከ መጪው አርብ በርካታ ባንኮች ሊጨናነቁ ይችላሉ።