አጫጭር ዜናዎች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አጫጭር ዜናዎች

1.ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ የፍርድረ ብይን መሰጠቱን ተከትሎ ከነሃሴ 14, 2008 ጀምሮ ዝዋይ/ባቱ የሚገኘው የፌደራል እስርቤት ተዛውረዋል። ብርሃኑ እና ፍቅረማርያም ቂሊንጦ በነበሩበት ወቅት ከነ በቀለ ገርባ ጋር በጭለማ ክፍል ከሌሎች እስረኞች ተለይተው እንዲቀመጡ መደረጋቸው የሚታወስ ነው። ዝዋይ ሄደን አግኝተናቸው እንደነገሩን ከሆነ እዛም ጨለማ ቤት ነው ያሉት። በቤተሰብ እና ጓደኛ መጎብኘት የሚፈቀድላቸው ሲሆን ጓደኞቻቸው እና ወዳጆቻቸው በሚመቻችሁ ቀን ሄዳችሁ ጠይቋቸው።
★★★★
2. በቃሊቲ የሴቶች እስር ቤት በቀጠሮ ክልል የምትገኘው ሃያተልኩብራ ነስረዲን እንዲሁም በፍርደኛ ክልል የምትገኘው መርየም ሃያቱ ከቤተሰብ እየተገናኙ አይደለም። ምክንያቱ ደግሞ እንዲለብሱ የተሰጣቸው ዩኒፎርም ነው።ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ቤተሰብ ሲገናኙ እና ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ዩኒፎርሙን መልበስ ግዴታ ነው። እንደሰማሁት ቀሚሱ እግራቸውን ስለሚያሳይ እና ከቀሚሱን ስር ደግሞ ታይትም ሆነ ማናቸውንም ነገር ማድረግ አይቻልም። ሂጃብ ማድረግ የሚቻል ሲሆን ኒቃብ ግን አይቻልም። በዚህ ምክንያት ቤተሰብ ሲያስጠራቸው እየወጡ አይደለም።
★★★★
3. ጫልቱ ታከለ ከ8 ዓመት እስር በኋላ ከእስር ወጥታለች።በሽብር ወንጀል የተከሰሱ እና የተፈረደባቸው ሴት እስረኞች የሚደርስባቸውን መድሎ እና መገለል ተቋቁማ ፍርዷን ጨርሳ ነው የወጣችው። ጫልቱ የወለጋ ልጅ ስትሆን በ2000ዓም ከኦነግ ጋር አብሮ በመስራት ክስ ሲቀርብባት እና ስትታሰር የአአ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነበረች። ቃሊቲ በነበርኩበት ወቅት ቀጠሮ ላይ የነበርን እና ፍርደኛ የሆኑ እስረኞች የተለያየ ግቢ ስለምንኖር፤ ከጫልቱ ጋር በሰፊው ተገናኝቼ የማውራት እድሉ አልገጠመኝም። ሆኖም ቤተሰብ በምንገናኝበት ጥቂት ደቂቃዎች ስንገናኝ በመብቷ ጉዳይ የማትደራደር፣ ቆራጥ፣ሃይለኛ፣ ማንንም የማትፈራ ደፋር እና ጠንካራ መሆኗን አይቻለሁ።