በምእራብ ሀረርጌ የመንግስት ወኪል የሆኑት አስተዳዳሪ መስጅድ መቃጠሉንና ሁለት ሰዎች መገደላቸውን በማመን በአክራሪዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ አሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በምእራብ ሀረርጌ የመንግስት ወኪል የሆኑት አስተዳዳሪ መስጅድ መቃጠሉንና ሁለት ሰዎች መገደላቸውን በማመን በአክራሪዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ አሉ
ነዋሪዎቹ ቁጥራቸው ከ20 በላይ ሙስሊሞች መገደላቸውን ና ከ100 በላይ መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡
ቢቢኤን
ባሳለፍነው ነሃሴ 21 ቅዳሜ በምእራብ ሀረርጌ መሳላ መስጅድ ላይ አጋዚዎች ቦንብ ማፈንዳታቸው እና መስጊድ ማቃጠላቸውን ንጹሃንን መግደላቸውን መዘገባችንን ይታወቃል፡፡ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ተቸግረን የቆየን ቢሆንም ይህን አስመልክቶ በትላንትናው እለት የቪኦኤ የአማርኛው ክፍልና ኦሮምኛው ክፍል በሙስሊሞች ላይ የተወሰደውን አስከፊ ጭቆና አቅርብዋል፡፡
ችግሩ የተከሰተው በአማን እና ወልተሲስ ሲሆን ለቪኦኤ የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪ ከ20 ሰዎች በላይ መገደላቸውን፤መስጅዱ መቃጠሉን ገልጸዋል፡፡ ከመስጅዱ ቃጠሎ የተረፈውን ቆርቆሮ እና ሌሎች ነገሮችን የፀጥታ ሃይሎች መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በሚያሳዝን መልኩ በግፍ የተገደሉትን ሙስሊሞች እንኳን መቅበር ያልቻሉ ሲሆን ዘመዶቻቸውም በግፍ መታሰራቸው፤ የሞቱትንም የቀበሩት ታጣቂ ሚኒሻዎች መሆናቸው የአካባቢው ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ አሁንም በአካባቢው እስሩ መቀጠሉን እና መንቀሳቀስ የማይችሉ መሆናቸውን ነዋሪው አያይዘው አስረድተዋል፡፡
የመሰላ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሙሃመድ አብዱረህማንን ቪኦኤ ያነጋገራቸው ሲሆን ርምጃ የተወሰደባቸው አክራሪዎች ናቸው ኦነግ፤ግንቦት ሰባት፤ የላካቸው ናቸው ሲሉ ሙስሊሞችን ወንጅለዋል፡፡ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል፡፡ የፈረሰው መስጅድም የአክራሪዎች ነው ሲሉ ወንጅለዋል፡፡
ይህም የሚያሳየው መንግስት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብነቱን ባሻገር በአማኞች ላይ እየፈጸመ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ነው ሲሉ የኮነኑት አስተያየት ሰጪዎች የወሰረዱት ርምጃ አልበቃ ብሎ በአክራሪዎች ላይ የተወሰደ ርምጃ ነው ማለታቸው ለህዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳያል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
መንግስትም ወደፊት ይህን አስመልክቶ አሸባሪዎችን ገደልኩ የሚል ድራማውን ለመስራት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ማህበረሰቡም ይህንን የተለመደ የመንግስትን ድራማ መረዳትና ማክሸፍ እንዳለበት ተገልጸዋል
ሙስሊሙ ማህበረሰብም እየፈጸመበት ያለውን ብሄራዊ ጭቆና በጋራ በአንድነት መተጋልም ይኖርበታል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ለቢቢኤን አስረድተዋል፡፡ ቢቢኤን ተጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያቀርብ ይሆናል ፡፡