በጎንደር አብራጅራና በአምባጊዮርጊስ በተደረገው የወያኔ አጋዚ በጥይት ከቆሰሉት ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


'ከአምባ ጊዮርጊስ ቆስሎ የመጣ ወገን'

በጎንደር አብራጅራና በአምባጊዮርጊስ በተደረገው የወያኔ አጋዚ በጥይት ከቆሰሉት ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ። አይን እማኞች አብራጅራ የተገደሉና ብዙ የቆሰሉ ወገኖች መመልከታቸውን ገልፀውልኛል። ወገን ተረባርቦ ይድረስልን ብለዋል። በበረሃው ያለው ጦርነት እንደቀጠለ ነው።
ሙሉነህ ዮሃንስ
++++++++++++
ዛሬ በመተማ በተፈጠረው ሕዝባዊ ተቃውሞ የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ወደ ሕዝብ ቀጥታ በመተኮስ እስካሁን የተረጋገጠ 12 አማሮችን መግደሉንና የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
መተማ ከተማ የትግራይ ነጻ አውጪ ጦር በአማሮች ላይ የዘር ማጥፋት ለመፈጸም ወደ ህዝቡ ሲተኩስ ከ30 በላይ ወጣቶች ደግሞ እግሮቻቸውን በጥይት በምመታት እንዳቆሰላቸው ለማወቅ ተችሏል::
በመተማ የትግራይ ተገንጣይ መንግስት ደጋፊ የሆኑ የንግድ ድርጅቶች መቃጠላቸው ሲሰማ ሕዝቡም እስካሁን ቁጥራቸው በይፋ ያልታወቀ ወታደሮችን መግደሉም ተሰምቷል::
የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር የሆንችው የንግድ ከተማዋ መተማ ዛሬ በጭስ ታፍና ውላለች:: የትግራይ ነጻ አውጪ ጦር ወደ ሕዝቡ ቀጥታ መተኮሱን የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች በሁለት ሃገራት መካከል የሚደረግ ጦርነት ይመስል ነበር ብለዋል::

'ከአብራጅራ ቆስሎ የመጣ'
'ከአብራጅራ ቆስሎ የመጣ'