ለኢትዮጵያውያን ምሁራንና ሊቃውንት የፊርማ ማሰባሰቢያ ጥሪ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሠተው ጉዳይ ላይ የሕዝባዊ ማስታወቂያ ጥሪ ከአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ የሰብእና [humanities]ና፣ የማኅበራዊ[social sciences]፣ እንዲሁም የሳይንስ [sciences] ጥናቶች ሊቃውንትና ምሁራን የሆኑት ኢትዮጵያውያን ባገራችን ውስጥ የተፈጠሩት አንገብጋቢ የፖለቲካ፣ የሰብኣዊ መብት፣ የምጣኔ-ሀብትና የማኅበራዊ ኑሮ ከፍተኛ ቀውሶች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ አቤቱታ ለማቅረብ፣ ከላይ የተጠቀሰው ኮሚቴ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ኮሚቴው በውጭ የምትኖሩት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ ከዚህ በታች በሚገኘው ድረ-ገጽ ገብታችሁ ፊርማችሁን በማስፈር ላገራችሁና ለወገኖቻችሁ ስትሉ ድጋፋችሁን በማበርከት በአቤቱታው እንድትተባበሩን በአክብሮት ይጠይቃል። የአቤቱታው ቅጂ፣ እንዳስፈላጊነቱ ተስተካክሎ፣ ለአሜሪቃ ፕሬዚደንት [USA President]፣ ለአውሮጳ አንድነት ሸንጐና[European Union Parliament] ለአውሮጳ አንድነት የሰብኣዊ መብቶች ጉዳይ ወኪል [European Union Commission for Human Rights] ይላካል። ቅጹን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በሚከተለው መልክ እንድትሞሉት በጥብቅ እናሳስባለን ።
Sign this petition [እውነተኛ ሳይሆን ለምሳሌነት/ለናሙና ብቻ የተሰጠ]
Full Name፡ [Dr., Professor etc ] Gabremaryam Paulos, [PhD, JD,MD etc] ማዕርግዎን እንዳስፈላጊነቱ ከፊት ወይንም ከኋላ ያስገቡት ። ]
Location: University of Manchester, UK [ያገር ስም ሳይሆን፣ የሥራዎን ድርጅት/ተቋምና ያለበት ቦታ/አ ገር ።]
Email : [email protected] [የ ድርጅት ዎን/ የ ተቋምዎን ኢሜይል ቢያስገቡ ይመረጣል ።]
ማሳሰቢያ። ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ባንዱም ላይ ማለትም ስምዎና ማዕርግዎ፣ የሥራዎ ቦታና ተቋም፣ እንዲሁም ኢሜይል ስሕተት ወይንም ሐሰት ሁኖ ቢገኝ ወይንም ጥርጣሬ ካለባቸው የአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴው ፊርማውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድረ-ገጹ አድራሻ እንደሚከተለው ነው → petitionbuzz.com