አገው ምድር የቻግኒ ወጣቶች ከወያኔ ቅልብ ነፍሰ ገዳዮች ጋር ፊት ለፊት ተፋጠዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጎጃም አገው ምድር የቻግኒ ወጣቶች ወደ ከተማው እየገባ ካለው የወያኔ ቅልብ ነፍሰ ገዳዮች ጋር ፊት ለፊት ተፋጠዋል። ወጣቶቹ የከተማይቱን መግቢያና መውጫ በሮች በድንጋይና በእንጨት እየተዘጉ ነው። ቻግኒዎች ከእንግዲህ ለወያኔ አንገዛም ብለዋል መላው የአገው ምድር ዛሬ ለሁለተኛ ቀን የዐማራን ተጋድሎ እያካሄድ ነው። ዳንግላና ቻግኒ ከተሞች ግንባር ቀደም ሆነዋል።
በመራዊ አንዲት እህት ተስውታለች፤ በጉማራ ሌሊቱን ሦስት ግብሬዎች ሲሰዉ ቁጥራቸው ያልታወቀ የመከላከያ ሠራዊት ተገድለዋል። ጋይንት አገዛዙን አባሮ ሕዝብ ከተማውን ይዟል። ደ/ታቦር ትናንት 2 ዐማሮች ተሰውተውብናል። አንዳቤት እስከ ጃራ ገዶ ያልው 10 ኪሎ ሜትር መንገድ ሕዝብ ተቆጣጥሮታል።