ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር የሚወስደውን ድልድይ ሰልፈኞች ዘግተውታል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አማራ ተጋድሎ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።
ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር የሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘውን ደምበጫ ድልድይ ሰልፈኞች ዘግተውታል። የመንገድ መዝጋቱ ዓላማ የወያኔን ኢኮኖሚ ለማዳሸቅ ነው። የመንገድ መዝጋቱ እንቅስቃሴ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በነዳጅ እጥረት ምክንያት በቅርብ ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ አይኖርም።
እንዲሁም ከባህርዳር ወደ አ.አ የሚያስገባው ሙሉአለም ችግኝ ሀሙሲት ላይ ተዘግቷል::
ብዙ የወያኔ ታፔላወች ተሰባብረዋል።”ወያኔ ሌባ” “ወያኔ ሌባ” ደምቆ የስተጋባል ሰልፈኞች ያስተጋቡት ጩኸት ነበር። የገብያ ቀን ቢሆንም አርሳ አደሮች ወደ ከተማ እንዳይገቡ በሚሊሻዎች ታግደዋል። በርካታ ወጣት እየጨፈረ ነው።ከተለያዬ ሰፈር ሰልፉን ለመቀላቀል አሁንም ህዝቡ እየተመመ ነው