ከ200 በሚበልጡ ባለስናይፐር የትግሬ መከላከያ ሠራዊትና በዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ መካከል ጎንደር አንገዘረብ ማረሚያ ቤት አካባቢ ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከ200 በሚበልጡ ባለስናይፐር የትግሬ መከላከያ ሠራዊትና በዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ መካከል ጎንደር አንገዘረብ ማረሚያ ቤት አካባቢ ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡ #AmharaResistance #MinilikSalsawi
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ይዘው ለመሔድ በፈለጉ የትግራይ መከላከያ ሠራዊትና በዐማራው ፖሊስ መካከል የተፈጠረውን ፍጥጫ የጎንደር ወጣቶች ተቀላቅለውታል፡፡ኮሎኔል ደመቀን እና የጎንደር ማረሚያ ቤት በአሁኑ ሰአት By Muluken Tesfaw (ትግሬን ከከተመው አስወጥቶ ዐማራን ለመጨረስ የታሰበ እቅድ) ከሁለት መቶ በሚበልጡ ባለስናይፐር የትግሬ መከላከያ ሠራዊትና በዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ መካከል ጎንደር አንገዘረብ ማረሚያ ቤት አካባቢ ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ይዘው ለመሔድ በፈለጉ የትግራይ መከላከያ ሠራዊትና በዐማራው ፖሊስ መካከል የተፈጠረውን ፍጥጫ የጎንደር ወጣቶች ተቀላቅለውታል፡፡ ብዙ ወጣቶች መንገዶችን እየዘጉና በዐማራ ፖሊስ በኩል መከለካያ ሠራዊትን ፊት ለፊት መጋፈጣቸውን ነው የሠማነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ውስጥ የምናገኘው እስረኛ አለ በሚል ሰበብ ማረሚያ ቤት እንገባለን ብለው የማረሚያ ቤት አስተዳደሩን ጥያቄ አቅርበው ትጥቃቸውን አስቀምጠው እንዲገቡ ተነገራቸው፡፡ ሆኖም ትጥቅ ውጭ ትተው ለመግባት ባለመፈለጋቸው እንዳይገቡ ተደርጓል፡፡ የጎንደር ማረሚያ ቤት እስረኞችም ኮሎኔልን አሳልፈን አንሰጥም በሚል አድማ እንዳደረጉ ለማወቅ ችለናል፡፡

ጥቂት የተኩስ ድምጽ የተሰማ ቢሆንም ከየትኛው በኩል እንደተተኮሰ የታወቀ ነገር የለም፡፡ በተያያዘ ግን አዘዞ አካባቢ የከተማው አውቶቡስ የቤት ውስጥ አድማውን ችላ ብሎ በመመላለሱ በድንጋይ ሲደበደብ የዐማራ ፖሊስ ወደ ሰማይ ጥይት በመተኮስ ችግሩን ለማብረድ ሞክሯል፡፡ አንድ ሌላ የመከላከያ መኪናም አብሮ በድንጋይ መሰባበሩን ለማወቅ ችለናል፡፡ አሁን ላይ የአዘዞ ወጣቶች ኮሎኔል ደመቀን ለማዳን ወደ ማረሚያ ቤቱ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በስልክ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡
የትግራይ መንግሥት የትግራይ ተወላጆችን ካስወጣ በኋላ ጎንደር ከተማን ዳግም የማተራመስ እቅዱን እያከናወነ እንደሆነ ነው ያነጋገርናቸው ሰዎች የገለጹት፡፡ የትግራይ ተወላጆች አስቀድሞ በማስወጣት ዐማራውን ለመጨረስ የሚደረገው እንቅስቀሴ አካል ነው፡፡ ወያኔ የትግራይ ተወላጆችን በግዴታ እንዲወጡ እንደተደረጉ አስመስሎ የአልጀዚራው ጋዜጠኛ ገንዘብ ከፍሎ ማሠራቱ የሚታወቅ ነው፡፡