ሰበር ዜና፤ ወያኔ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን አፍኖ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምሯል፣የጎንደር ሕዝብ ለወገኖቹ የድረሱልን ጥያቄ አቅርቧል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወያኔ ታላቁን የዘመናችን ጀግና ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን አፍኖ ለመውሰድ ከፍተኛ ዝግጅትና ወታደራዊ ከበባውን በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባቱን ከጎንደር የደረሰን ዜና ያመልክታል። ወያኔ ከውጭ ወራሪ ጦር ጋር ለመጋፈጥ የማይተናነስ እጅግ የታጠቀና በዘመናዊ የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቀ ከትግራይ የመጣ ጦር ኮሎኔል ደመቀን አፍኖ ለመውሰድና አሰቃይቶና አዋርዶ ለመግደል እንቅስቃሴ ጀምሯል። የጎንደር ሕዝብ ለመላው ወገኑ ኢትዮጵያዊ የድረሱልን ጥሪ እያሰማ መሆኑም ታውቋል። ድል አለመስዋዕትነት እንደማይገኝ አበክረው የሚያውቁት ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ በጀመሩት የብሔራዊ አርነት ንቅናቄ በመስዋዕትነት ቢያልፉ፣ ሁልቆ መሳፍርት የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን አርማቸውን አንግበው ትግሉን ፍጻሜ በማድረስ ወያኔን እንደሚደመስሱት ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው። በዚህ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።

https://www.youtube.com/watch?v=5vBT03wPku8