ወያኔ ሆይ (ሰልፍ?) እስኪ ሞክራትና እናሳይሃለን። በገዛ ኣገሩ ኣንዱ ባዳ ኣንዱ ባለጓዳ ኣይሆንም።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያውያን እስር ግድያ እንጂ ሌላ የተለየ ችግር ኣይገጥመውም የሚል ማስፈራሪያ ይሁን ማስተባበያ የማይታወቅ የጅሎቹን የወያኔ ሚዲያዎች ዜና በሰማን በሰኣት ልዩነት የኢሕ አዴግ ጽ/ቤት ምንጮቻችን ስብሰባ ይሁን ሰልፍ የምንጠራው በሚል የወያኔ ሰዎች ውይይት መያዛቸውን ሰማን፤ እና ወያኔ ሆይ ስብሰባ ይሁን ሰልፍ እስኪ ሞክራትና እናሳይሃለን። በገዛ ኣገሩ ኣንዱ ባዳ ኣንዱ ባለጓዳ ኣይሆንም።
በኦሮሚያ ክልል እና በኣማራ ክልል የሚያካሄዱ የሕዝብ ተቃውሞዎችን ለማውገዝ በሚል ሕወሓት/ ኢሕአዴግ በኣዲስ ኣበባ መስቀል ኣደባባይ ኣባላቱንና ደጋፊዎቹን እንዲሁም የኣዲስ ኣበባን ሕዝብ ስብሰባ ይሁን ሰልፍ ለማስወጣት በፓርቲው በተዋረድ የውይይት ስራዎች መጀመራቸውን ኣዲስ ኣበባ ከሚገኘው የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የሚገኙ ምንጮች ኣረጋግጠዋል።
ስለዚህ ይህንን ወያኔ ራሱ በሚጠራው ስብሰባ ይሁን ሰልፍ ላይ ራሱ ወያኔን በማውገዝ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማት ስለሚቻል የኣዲስ ኣበባ ሕዝብ ለዚሁ ተቃውሞ እንዲዘጋጅ ኣስፈላጊውን ስራዎች ሁሉ የለውጥ ሃይሉ መስራት ኣለበት።በራሱ ገበታ ላይ ራሱ ይዋረዳል ወያኔ መግቢያ እስኪጠፋው ድረስ በሚጠራው ስብሰባ ይሁን ሰልፍ ላይ እናሯሩጠዋለን። በለውጥ ሃይሉ በኩል ሰፊ ስራ የሚሰራበት ወቅት ላይ ነን። #ምንሊክሳልሳዊ