በሪዮ ኦሎምፒክየማራቶን ውድድርን በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ እጁን ከፍ አድርጎ በማጣመር የተቃሞ ምልክት ያሳየው ፈይሳ ሌሊሳ የኢትዮጵያ መንግስትን ተቸ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በሪዮ ኦሎምፒክየማራቶን ውድድርን በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ እጁን ከፍ አድርጎ በማጣመር የተቃሞ ምልክት ያሳየው ፈይሳ ሌሊሳ የኢትዮጵያ መንግስትን ተቸ
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=JFRt1Aaml_w]

በሪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ሌሊሳ የማራቶን ውድድርን በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ እጁን ከፍ አድርጎ በማጣመር በኢትዮጵያ ተቃውሞዎች በብዛት የሚስተዋለውን ምልክት አሳየ። ፈይሳ የማራቶን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2:09:54 የፈጀበት ሲሆን ኬንያዊው ኢልዩድ ኬፕቾጌ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል።
ፈይሳ ከውድድሩ ካጠናቀቀ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-ምልልስ የኢትዮጵያ መንግስትን ተችቷል። «በእስር ላይ የሚገኙ ዘመዶች አሉኝ።» ያለው ፈይሳ «ስለ ዴሞክራሲ ካወራህ ይገድሉኃል።» ሲል አክሏል። የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊው ፈይሳ ሌሊሳ«ወደ ኢትዮጵያ ብመለስ ምን አልባት ይገድሉኝ ወይም ያስሩኝ ይሆናል።» ሲል ሥጋቱን ገልጧል።ፈይሳ የተቃውሞ ምልክቱን ከውድድሩ በኋላ ከአሸናፊዎቹ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ከጋዜጠኞች ፊት ደግሞታል። ውድድሩን ካጠናቀቀም በኋላ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ይዞ አልታየም።
«በአገሬ ያለው ሁኔታ አደገኛ ነው። ምን አልባት ወደ ሌላ ገር መሔድ ይኖርባኝ ይሆናል።» ያለው ፈይሳ «የተቃወምኩት በሁሉም ስፍራ ለሚገኙ ነጻነት ለሌላቸው ሰዎች ነው።»
ብሏል። ፈይሳ እጁን ያጣመረው «በአገሬ በመንግስት ለሚገደሉ ተቃዋሚዎች» ያለውን ድጋፍ ለmsኢ,ት እንደሆነም ተናግሯል። «በእዚያ ተመሳሳይ ምልክት ያሳያሉ» ያለው ፈይሳ «እየተደረገ ባለው ነገር እንደማልስማማ ማሳየት እፈልጋለሁ።በእስር ላይ የሚገኙ ዘመዶች እና ጓደኞች አሉኝ።» ብሏል ፈይሳ የኢትዮጵያ መንግስት ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎችን እየገደለ ነው ሲልም ወቅሷል። ፈይሳ ዓለም አቀፍ ትኩረት በሚስበው የማራቶን መድረክ ያሳየው የተቃውሞ ምልክት ፌስቡክና ትዊተርን በመሰሉ ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ተቸሮታል። ኢትዮጵያውያኑ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት የሆነውን የማራቶን አትሌት «ጀግና» ሲሉ አወድሰውታል።
«ኢትዮጵያ በርካታ ብሔሮች አሏት። አንዳንዶቹ በመንግስት መሬታቸውን ተቀምተዋል፤ተገድለዋል። ብሏል የማራቶን አትሌቱ። «ሰላም እና ዴሞክራሲ እንፈልጋለን።» ያለው ፈይሳ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ ተናግሯል። በአዲስ አበባ ለሚኖሩ ቤተሰቦቹ ደህንነት ስጋት እንደሚሰማውም ገልጧል።
Dw Amharic