የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ሴክሬታሪና ኮፒ ታይፒስቶች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች  Tadesse Biru Kersmo

ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ሴክሬታሪና ኮፒ ታይፒስቶች

“ሕዝባዊ አሻጥር” Civic Sabotage የሚለውን ለመተርጎም የጠቀምንበት ሀረግ ነው። ሕዝባዊ አሻጥር ለበጎ ዓላማ ሲባል፤ አምባገነን አገዛዝን ለማዳከም የሚደረግ፤ ከሥነ ምግባር አንፃር ተቀባይነት ያለው፤ ጠላትን በስውር ማፍረሻ ዘዴ ነው። ህወሓትን ለማዳከም እያንዳንዱ ጠጠር ይወርውር። ሕዝባዊ አሻጥር እያንዳንዱ ዘዴ በሥራና በመኖሪያ ቦታው ሊተገብረው የሚችል የትግል ዘዴ ነው። ይህ አጭር ጽሁፍ የተዘጋጀው ግን በተለይ ለሴክሬታሪና ኮፒ ታይፒስቶች ነው።

በመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ድርጅት ውስጥ በኤዜክቲቭ ሴክሬታሪነት፣ በሴክሬታሪ ታይፒስትነት ወይም ኮፒ ታይፒስነት የሥራ መደብ ላይ ተቀጥረሽ በመሥራት ላይ የምትገኚ ኢትዮጵያዊት ወገን ሥራሽን ሳትለቂ ከህወሓት አገዛዝ ለመላቀቅ የሚደረገውን ትግል ከብዙ ሌሎች ሰዎች ይበልጥ ማገዝ ትችያለች። ለዚህ ሁለት አማራጭ መንገዶች አሉሽ: (1) ታማኝና ታታሪ መምሰል፣ እና (2) መለገም።

1. ታማኝና ታታሪ ሠራተኛ መምሰል የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት (ሀ) ታማኝ መምሰልሽና ታታሪነትሽ በአለቃሽ ክብርና ሞገስ ያሰጥሻል፤ (ለ) በቅርብ አለቃሽ ሞገስ ማግኘትሽ የቅርብ አለቃሽን ብቻ ሳይሆን የሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን እና የአለቃሽ አለቆችን ምስጢር የማወቅ እድል ይሰጥሻል፤ (ሐ) ለአደጋ የመጋለጥ እድልሽ አነስተኛ ነው፤ እና (መ) የደረጃ እድገት የማግኘት እድልሽ ከፍተኛ ነው። ሆኖም ግን ታማኝና ታታሪ ሠራተኛ መምሰል የሚከተሉት ጉዳዮች አሉት: (ሀ) በሕዝብ ዓይን የወያኔ ታማኝ ሎሌ ነሽ፤ ይህ ደግሞ ህሊናሽን ሊረብሸው ይችላል፤ (ለ) የምታወጫቸው ምስጢሮች ወዲያውኑ የሚታይ ለውጥ ካላመጡ ተስፋ ሊያስቆርጥሽና ምነው ባላወቅሁት ሊያሰኝሽ ይችላል፤ እና (ሐ) ራስሽን አሳምነሽ ካልተነሳሽ ለገዳይ ሥርዓት ተግተሽ እየሠራሽ በመሆኑ ንፁሁ ህሊናሽ እና አስመሳዩ ተግባርሽ ይጣሉብሻል።

2. መለገም የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት (ሀ) የማታምኚበትን ነገር በቶሎ ተፈፃሚ እንዳይሆን በማስተጓጉልሽ፤ “ምን አገባኝ” ሳትይ በተቻለሽ አቅም ይህንን አፋኝ ሥርዓት በመታገልሽ መንፈሳዊ ርካታ ይሰጥሻል፤ (ለ) የሥራዎችሽ ውጤት ወዲያው የሚታይ ነው፣ እና (ሐ) በፀረ – ወያኔ አቋምሽ የማኅበረሰብ ክብርና ሞገስ ታገኛለሽ፤ ስለታዘዝሽ ብቻ የማታምኚበትን የማትሠሪ በመሆንሽ ለራስሽ ህሊና ብቻ ሳይሆን ለወዳጆችሽና ወገኞችሽ ኩራት ነው። ሆኖም ግን ይህ አማራጭ ለአደጋ የተጋለጠ ነው፤ በግምገማዎች ወቅት ትችት ማስተናገድ የማይቀር ነው።

1. ታማኝና ታታሪ በመምሰል ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች

1.1. በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ፣ በፌደራል ሚኒስትሮች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በፌደራልና በክልል ፓሊስ ተቋማት እና በመንግስት የልማት ድርጅቶችና ተቋማት ውስጥ በኤክዜክዩቲቭ ሴክሬታሪነት፣ በሴክሬታሪ ታይፒስትነት ወይም በኮፒ ታይፒስትነት የምትሠሩ ወገኞቻችን ከፍተኛ ኃላፊነት አለባችሁ። በሕዝብና በአገር ላይ እየተፈፀሙ ያሉ በደሎችን ከጥንስሳቸው ጀምሮ ታውቃላችሁ። በሺህ ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን እስርና ሞት፣ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ውሳኔዎች በእናንተ ኮምፒተሮችና ስልኮች በኩል አልፏል። ለመረጃ ያላችሁ ቅርበት የእናንተ ጉልበት ምንጭ ነው፤ በአግባቡ ተጠቀሙበት። ታማኝና ታታሪ መስላችሁ በመሥራት የህወሓት አገዛዝን መሠሪ እቅዶችን አስቀድሞ በማውጣት ሕይወት ማዳንና አገርን መታደግ ትችላላችሁ።

1.2. ታማኝና ታታሪ ሠራተኝነትሽ የቅርብ አለቃሽን ብቻ ሳይሆን የሌሎች በተመሳሳይ ደረጃ ያሉ ባለሥልጣኖችን ከዚያም አልፎ የአለቃሽ አለቃንም ምስጢሮች የማወቅ እድል ይሰጥሻል። እነዚህን መረጃዎች ሁሉ እጅሽ ውስጥ አድርጊ። ቃለጉባኤዎች፣ ሪፖርቶች፣ የተለያዩ ሰነዶችና የደብዳዴ ልውውጦች ቅጂ ከቢሮሽ ኮምፒዩተር ውጭ ማስቀመጥ ልመጂ። ይህን ለማድረግ ሞባይል በጣም አመቺ ነው፤ ሞባይልሽ ሚሞሪ ካርድ ይኑረው። ሞባይላሽን ቻርድ እያደረግሽ እግረ መንገዱን ፋይሎችን ከኮፒዩተር ወደ ሞባይል ካርድ አስተላልፊ፤ ጊዜ አይወስድም፤ external hard disc ወይም flash card አያስፈልግም። ከውጭ ተጽፈው የሚመጡትን ደብዳቤዎችም በዚያው ሞባይልሽ ፎቶ አንሻቸው። እነዚህ ማስረጃዎች ለነፃነት ኃይሎች እንዲደርስ አድርጊና ሞባይልሽን አጽጂ። “መረጃዎችን የት ልላክ?” የሚለው ጥያቄ ብዙ የሚያስጨንቅ አይደለም፤ በርካታ አማራጮች አሉ። ለምሳሌ ከዚያው ከሞባይል በፌስ ቡክ መልዕክት ለኔ መላክ ይቻላል፤ ለኢሳት መላክ ይቻላል፤ አስቀድሞ በመነጋገር የተለየ የመረጃ ቋት ማዘጋጀት ይቻላል። አንዴ ግኑኝነት ከተፈጠረ በኋላ አማራጭ መስመሩ ብዙ ነው፤ email, viber, imo, whatsapp, dropbox, … etc. መጠቀም ይቻላል። በአምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ ስም ቀይሮ ፌስ ቡክ፣ ኢሚል፣ … ማውጣት አንዳችም ነውር የለበትም። የህወሓት ሹማምንትም በውሸት ስማቸው ነው እስካሁን የሚጠሩት።

1.3. የሥራሽ ባህሪና ታማኝነትሽ ብዙ መረጃዎች እጅሽ ውስጥ እንዲገቡ ያደርግና የትኞቹ ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ መወሰን ሊቸግርሽ ይችላል። የሚከተለውን ዝርዝር ለመረጃዎች መረጣ ፍንጭ ይሰጥሻል።

1.3.1. “እጅግ በጣም ብርቱ ምስጢር፣ ብርቱ ምስጢር ወይም ምስጢር” የሚል ደረጃ የተሰጣቸው ደብዳቤዎች፣
1.3.2. የምስጢር ደረጃ ባይወጣላቸውም ፓሊሲና ገንዘብ ነክ የሆኑ የደብዳቤ ልውውጦች፣
1.3.3. ሁሉም ቃለጉባኤዎች፣
1.3.4. ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ ሪፓርቶች፤ የኦዲት ሪፓርቶች፤ የግምገማ ሪፓርቶች፤ … ወዘተ
1.3.5. ጥናታዊ ጽሁፎች፤ የስልጠና ማንዋሎች፤ ኮሚኒኬዎች፣ … ወዘተ
1.3.6. የባለሥልጣኖችን የሞባይል፣ የቤትና የቢሮ ስልክ ቁጥሮችና የኢሜል አድራሻዎች። በመሥሪያ ቤቱ ያሉ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድና የደህዴድ አባላት የሞባይል፣ የቤትና የቢሮ ስልክ ቁጥሮችና የኢሜል አድራሻዎች፤
1.3.7. በመሥሪያ ቤቱ ያሉ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድና የደህዴድ ህዋሳት ስብሰባዎች ቃለጉባዬዎች።

1.4. ታታሪነትሽና ታማኝነትሽ ለአገዛዙ የተሳሳተ መረጃ ለመስጠትም አመቺ ነው። ጠላትን ማሳሳት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው የትግል ስልት ነው። ለአለቃሽ የተሳሳተ መረጃ ለመስጠት ያንቺን ያህል የተመቸ ሰው ላይኖር ይችላል።

2. በመለገም ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች

2.1. ለቢሮ አገልግሎት በሚታዘዙ እቃዎች፣ በሚባዙ ቅጂዎች እና በማናቸውም ጉዳይ በደብዳቤ ውስጥ የሚሰፍሩ ቁጥሮችን ስትጽፊ “ተሳስተሽ” ከበስተጀርባው 0 ወይም ሌላ ቁጥር ጨምሪ፤ ወይም አንድ ቁጥር “እርሺ”። ተቀራራቢ ስሞችን አዛቢ። ደብዳቤዎችን ስትልኪ አድራሻዎችን አዛብተሽ ላኪ፤ ለምሳሌ፣ የመከላከያውን ለጤና ጥበቃ፤ የትግራዩን ለጋምቤላ፤ ለፓሊስ የተፃፈውን ወደ ሆስፒታል .. ወዘተ. ላኪ።

2.2. ታይፕ ስታደርጊ መሠረታዊ ቃላትን አዛቢ፤ መሳሳት ያለ ነውና ተሳሰች። ለምሳሌ “ጥይት” የሚለውን ቃል “ጥቂት” ብለሽ ታይፕ አድርጊ፤ “ግብርና” በማለት ፋንታ “ግርድና”፤ “የአገር ደህንነት” በማለት ፋንታ “የአገር ድህነት” እያልሽ ፃፊ። ቃላቶችን ማዛባት መዝናኛሽ አድርጊ።

2.3. ሥራሽን በጊዜ ለመጨረስ አትትጊ። ባለጉዳዮችን ለማስተናገድ አትቸኩይ፤ ጉልበትሽህን ቆጥቢ። ከበላይ አካላት ጋር ያለው የደብዳቤ ልውውጥ የተራዘመና የተንዛዛ እንዲሆን አድርጊ።

2.4. በጣም አስፈላጊ የሆኑ ዶሴዎችን አለቦታቸው አስቀምጪ፤ ለራስሽም ኮፒ ያዢና ለነፃነት ኃይሎች አስተላልፊ።

2.5. የሥራ ጊዜ አባክኝ። ሥራህን የሚያቋርጡ ነገሮችን ፍጠሪ። የስቴፕለር ሽቦ መቀየርም ቢሆን ዘለግ ያለ ጊዜ ይውሰድብሽ። ሥራ ቢወዘፍ ወይም ባለጉዳይ ቢጉላላ አይጭነቅሽ “ሥራ ላይ ነሽና”።

2.6. “ሥራሽ ጥራት የጎደለው ነው” የሚል ትችት ከመጣ አትደናገጪ። ይልቁንም የመሥሪያ ቤቱ ድክመት አንቺን ማሠራት እንዳልቻለ አስረጂ። የኮፒተሮቹና ማባዣዎቹ አለመሥራት፤ ወረቀቱ ጥራት የጎደለው መሆኑ፤ ቢሮሽ ለሥራ ምቹ አለመሆኑ፤ ሠርቶ የሚያሠራ ኃላፊ የሌለ መሆኑ፣ … ወዘተ. ለሥራሽ ጥራቱ መጓደል ምክንያት ይሁኑ።

2.7. የአለቃሽ አለቆች ወይም ባልደረቦች አለቃሽን ፈልገው ሲደውሉ በትህትና “አጣዳፊ ሥራ ላይ መሆናቸውን” ንገሪያቸው ወይም “ሌላ ስልክ ይዘዋል” እያልሽ በትህትና አጉያያቸው።

2.8. አወዛጋቢ ጭምጭታዎችን “በውስጥ አዋቂነት” አሰራጭ።
***