በደቡብ ኦሞ–ጂንካ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በደቡብ ኦሞ–ጂንካ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል //

ከዚህ በፊት በደቡብ ኦሞ ዞን አርሶአደሩ ማዳበሪያ አልወስድም፣ ብድር አልከፍልም– የግብርና ልማት ኤክስቴንሽን ሰራተኛ/ ዲኤ/ ግብር ሰብሳቢ አይደለምና ያለስራችሁ አትግቡ፣ አትምጡብን በማለት የማዳበሪያ ዕዳና ግብር አንከፍልም ማለታቸውን ከዞኑ ነዋሪዎች መገለጹ ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ በዚህ ወር አርሶአደሩ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዕረፍት ወደአካባቢያቸው ተመልሰው የገጠሩን ህዝብ ለማነጋገር ወደተለያ የገጠር ቀበሌዎች ያመሩት አቶ አሸናፊ ጋዕሚ መጀመሪያውኑ መቼ መረጥንህ፣ የት ስናውቅህ ነው … ዓመት ስታንቀላፋ ነበርንጂ በዞናችን ስላሉ ችግሮች ምን አንስተሃል…. ምን ስታደርግ እንደቆየህ ማን ያውቅልሃል ብለው የጠራውን ስብሰባ በትነው ያለአንዳች ውጤት በሄደበት እግሩ መልሰውታል፡፡
‹የተከበሩ› አቶ አሸናፊ ጋዕሚ ‹‹ በመልካም አስተዳደርና የዞኑ/ጂንካ ልማት›› ዙሪያ ህዝብ ለማነጋገር ነሃሴ 09/08 በጂንካ ከተማ የጠሩት ስብሰባም ከገጠሩ ህዝብ የተለየ ምላሽ አላገኘም፣ በስብሰባው ከተገኘው 200 ያህል ህዝብ ከ150 በላይ ስብሰባውን ረግጠው አቶ ዓለማዬሁ ከዞኑና የከተማው ባለሥልጣናትና ካድሬዎች ጋር በአዳራሹ ቀርተዋል፡፡

ተሰብሳቢዎች ስብሰባውን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በሰጡት አስተያየት — እኛን ከመሰብሰባችሁ በፊት ከራሳችሁ አልፋችሁ እኛን ጭምር ‹‹ የትግሬ አሽከርና አጃቢ አድርጋችኁናል›› ፤ ራሳችሁን ‹ከትግሬ አሽከርነት አውጥታችሁ›› ተመለሱ በማለት ለዚህም– በዞናችን የምንገኝ አልሚዎችንና ኮንትራክተሮችን የምትፈልጉን እነርሱን ‹‹እንድናጅብላችሁ በአጨብጫቢነት›› ነው፡፡ ለምሳሌ ለጂንካ ኤርፖርት ግንባታ እኛን አጫርታችሁ ስታበቁ ዞኑን የማያውቀውን ‹‹አፍሮጽዮን ›› የሚባል ኮንትራክተር ከትግራይ ጠርታችሁ ሰጣችሁ፣ ዛሬ ለዩኒቨርስቲ ግንባታም ተመሳሳይ ለማድረግ እንደማትመለሱ ፍንጮች እየታዩ ነው፡፡ በተጨማሪ ከዚህ በፊት ያዋጣነውን የልማት ገንዘብ መብላታቸው በግምገማ ተረጋግጦ ‹‹ ይከሰሳሉ፣ ለፍርድ ይቀርባሉ ›› ያላችሁን የወቅቱ የዞኑ አስተዳዳሪ እነ-ካይዳኪ ገዛሃኝ ( አሁን የፈዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ሃላፊ) ዛሬ የት እንደሚገኙ እናውቃለን፤ አሁን ደግሞ ለየትኛው ተረኛ ነው ገንዘብ አዋጡ የምትሉን? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል የአስተዳደሩ ደጋፊ ነጋዴ ዓሊ ሰይድ ‹‹ በከተማም ሆነ ገጠር ህዝቡ መንግስት የለም ብሎ እንደፈለገው እየሆነ ነው፤ ይህን የሚያውጀው ኢሳት ነው፡፡ በእርግጥ መንግስት የለምንዴ– ካለ ለምን ኢሳትን አይዘጋልንም ? ›› ሲሉ ተማጽነው በህዝብ ትዝብት አትርፈዋል ፡፡
ህዝቡ ሁኔታዎች በዚህ መልክ ከቀጠሉ እናም እንደኦሮሚያና አማራ ህዝብ ወደአደባባይ መውጣችን አይቀርም ብለዋል፡፡